መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 5፤2016 –እስራኤል ሰላማዊ ሰዎች ከፍልስጤም እንዲወጡ የተኩስ አቁም ጥያቄ ቢቀርብላትም ዉድቅ አደረገች

እስራኤል ሰላማዊ ሰዎች ከፍልስጤም እንዲወጡ የተኩስ አቁም ጥያቄ ቢቀርብላትም ዉድቅ ማድረጓ በአለማቀፍ መገናኛ ብዙኃን በመዘገብ ላይ ይገኛል።

ሐማስ እና እስራኤል በደቡባዊው የፍልስጤም ክፍል ተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማምተዋል መባሉን ያጣጣሉ ሲሆን የተኩስ አቁሙ አላማ ሰላማዊ ፍልስጤማዉያን እና የዉጭ ሀገር ዜጎችን ወደ ግብፅ ለማሻገር ያለመ ነበር።

በፍልስጤም በጦርነቱ እስካሁን ቁጥራቸዉ ከ 1 ሺህ በላይ ሰዎች የገቡበት አለመታወቁን አልጀዚራ የዘገበዉ ሲሆን በፍርስራሾች ዉስጥ ይሆናሉ ተብሎ ይገመታል ተብሏል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በበኩሉ የፍልስጤም ሆስፒታሎች የሀይል መጠባበቂያ ጄነሬተር ነዳጅ በጥቂት ሰዓታት ዉስጥ ይጨርሳሉ ብሏል።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *