የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ዋና ፀሀፊ አንቶኒ ብሊንከን ከአራት ቀናት በኋላ በድጋሚ ለውይይት ቴላቪቭ ከተማ ገብተዋል።
በጋዛ ጦርነት ላይ የሚያደርጉትን ውይይት ለመቀጠል በኢየሩሳሌም ከሚገኙ መሪዎች ጋር ለመምከር መመለሳቸው ተሰምቷል። ብሊንከን አሜሪካ ለእስራኤል ያላትን ድጋፍ ለማሳየት ሐሙስ እለት ወደ ቴል አቪቭ ማቅናታቸው የሚታወስ ሲሆን ከዛም ወደ ስድስት የአረብ ሀገራት ተጉ፣ነው ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶችን አድርገዋል።
ፕሬዝዳንት ባይደን ከእስራኤል ግብዣ ከተደረገላቸው በኋላ በሚቀጥሉት ቀናት እስራኤልን ይጎበኛሉ የሚል ግምት አለ።የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ዋና ፀሀፊ አንቶኒ ብሊንከን ቴል አቪቭ ዳግም ወደ እስራኤል መመለስ የዚህ ጦርነት ቀጣናዊ መባባስ እና በተለይም የኢራን ትልቁ አጋር የሆነው ሂዝቦላህ ጉዳይ በጣም አሳሳቢ አድርጎታል።
አሜሪካ አስደናቂ በሆነ መልኩ የሃይል ክምችቷን ወደ ሜዲትራኒያን ባህር እያሰባሰበች ይገኛን።ምንም እንኳን እስራኤል እራሷን ለመከላከል ሁል ጊዜ ከአሜሪካውያን ድጋፍ ብታገኝም በዚህ ጊዜ ግን የተደረገው ድጋፍ ከፍተኛ ሆኗል ። ብሊንከን እንዳሉት እስራኤል “ትክክለኛው መንገድ” ብቻ መከተል እንዳለባት ከአሜሪካውያን ተደጋጋሚ ማሳሰቢያዎች ተሰጥተዋል።
ምክንያቱም ፍልስጤማውያን ሰላማዊ ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ሞት መጨመር በአካባቢው ያለውን ውጥረት በማንገስ ቀጠናውን ሊረብሸው ይችላል።እስራኤል ኃይሎቿ ምን እንደሚሠሩ እና በጋዛ ውስጥ የት እንደሚሄዱ በትክክል መወሰን አለባት የሚሉ ጥሪዎች እየቀረቡ ይገኛል።
በጋዛ ከ 2.4 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ይኖራል።ሃማስ ከተወገደ ማን ተቆጣጥሮ ጋዛን ያስተዳድራል የሚለው ጥያቄ ምላሽ ያሻል። የሃማስ ተፎካካሪው እና የፍልስጤም ዌስት ባንክን የሚያስተዳድረው ፋታህ ሊመጣ ይችላል የሚል ግምት እየተሰጠ ቢሆንም ፋታህ በእስራኤል ይደገፋል የሚል ታማኝነት ከጎደለው ውጤታማነቱ አጠራጣሪ ይሆናል ።
እስራኤል ጋዛን ለመያዝ እንደማትፈልግ ብትገልፅም ነገር ግን ምንም አማራጭ ከሌለ ለተወሰነ ጊዜ ልትገደድ ትችላለች።
በስምኦን ደረጄ