
አንድ የሊትዌኒያ ዜግነት ያለው ግለሰብ የተመገበበትን ሂሳብ ላለመክፈል በሀገሪቱ በሚገኙ 20 ሬስቶራንቶች ከበላ እና ከጠጣ በኃላ የልብ ድካም እንዳለበት በማስመሰል ሲወድቅ በስፔን ውስጥ ተይዟል።
ስሙ ያልተጠቀሰው ይህው ሰው የ50 አመት ጎልማሳ ሲሆን እንዲህ ዓይነቱን ድራማ በማሳየት ቢያንስ 20 ምግብ ቤቶችን አጭበርብሮ እንደነበር ተዘግቧል። ምግብና መጠጥ ካዘዘ በኋላ በደንብ ይመገብ እና ደረቱን በመጨበጥ ራሱን የሳተ በማስመሰን ወለሉ ላይ ይወድቃል።
የማጭበርበር ድርጊቱ የታወቀበት ይህው ሰው በአንድ የምግብ ቤት ባለቤት ሲሆን ከዚህ ቀደም እንዲህ ዓይነት ድርጊት ሲፈፅም መመልከቱን እና በአካባቢው የሚገኙ ምግብ ቤቶች ፎቶግራፉን አሰራጭተው መመልከቱን በማስተዋሉ ነው። ለፎቶው መነሻ የሆነው ባለፈው ወር ይህው የሊቱዌኒያ ሰው በአሊካንቴ ከተማ በሚገኘው ኤል ቡኤን ኮሜር ሬስቶራንት ውስጥ ተገኝቶ ነበር።
የባህር አሳ እና ጥቂት ውስኪ ከጠጣ በኃላ 34.85 ዩሮ ወይም 37 ዶላር ሂሳብ በአስተናጋጁ ይመጣለታል።አስተናጋጁ ሸውዶ ለመውጣት ቢሞክርም ሳይሳካለት ይቀራል።በዚህ ጊዜ ነበር የልብ ድካም እንዳለበት ማስመሰል የጀመረው።
የኤል ቡን ኮሜር ምግብ ቤት ሥራ አስኪያጅ በድራማው በጣም በመናደዱ ድርጊቱን እንዲያቆም ፎቶውን ለሁሉም ምግብ ቤቶች በቴሌግራም ይልካል።ታዲያ መረጃው የደረሳቸው የሬስቶራንቱ ሰራተኞች በቲያትሩ ተደናግጠው አምቡላንስ ከመጥራት ይልቅ ለፖሊስ አሳውቀዋል።
የፖሊስ መኮንኖቹ ወደ ቦታው ሲደርሱ የታመመ የሚመስለው ሰው የሕክምና ዕርዳታ ጠብቆ የነበረ ቢሆንም የፖሊስ ካቴና ጠብቆታል። የስፔን መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት፣ የ50 አመቱ ሰው በኮስታ ብላንካ ሬስቶራንት ባለቤቶች ዘንድ በተወሰነ ደረጃ ታዋቂ ሆኗል። እ.ኤ.አ. በኖቬምበር 2022 እኛም ጋር ይህ ሰው እንደዚህ አድርጓል ሲል አንድ ምግብ ቤት ያስታወቀ ሲሆን በልብ ድካም በማጭበርበር ልማዱ ዝነኛ ነው ብሏል።
በደርዘብ የሚቆጠሩ ሬስቶራንቶችን በሀሰተኛ የልብ ጥቃቱ ከታለሉ በኋላ አጭበርባሪው ሰው ከእስካሁን የባሰ ትልቅ ፈተና ሊገጥመው ይችላል ተብሏል።በርካታ የምግብ ቤት ባለቤቶች ተባብረው በጋራ ቅሬታቸውን ለማቅረብ በማቀዳቸው ግለሰቡ እስከ ሁለት አመት እስራት ሊጠብቀው ይችላል ተብሏል።
በስምኦን ደረጄ