መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 6፤2016 –በኬንያ የህግ ትምህርት ሳይማር በፍርድ ቤት 26 የክስ መዝገቦችን ሀሰተኛ ጠበቃ በመሆን ያሸነፈው ግለሰብ መነጋገሪያ ሆኗል

አንድ ኬንያዊ ምንም አይነት መደበኛ ስልጠና ባይኖረውም ጠበቃ በመምሰል የተለያዩ ደንበኞችን በመወከል በ26 የክስ መዝገቦች ላይ ቢያሸንፍም በቅርቡ በቁጥጥር ስር ውሏል።ብራያን ምዌንዳ ንጃጊ በቲቪ ተከታታይ ሱትስ የተሰኘ ታዋቂ ገፀ ባህሪ ላይ እንደሚታየው በእውነተኛ ህይወቱ ማይክ ሮስ የሚል ስያሜ አለው።

ይህ ወጣት በከፍተኛ ደረጃ የህግ ድርጅት ውስጥ ለመስራት እና ደንበኞችን ለመወክል የሚያበቃው ነገር ባይኖረውም መደበኛ የሕግ ትምህርት ቤት ትምህርት ሳይከታተል ሲሰራ ቆይቷል። ምዌንዳ በ26 የተለያዩ ጉዳዮች ደንበኞቹን በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ዳኞች እና በከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ፊት መወከል መቻሉ አነጋጋሪ አድርጎታል።

ወጣቱ ራሱን እንደ ብቁ ጠበቃ አድርጎ ለማቅረብ ችሏል።የኬንያ የህግ ማኅበር  መጠራጠር የጀመረው ብራያን ምዌንዳ የተባለ ትክክለኛ የሕግ ባለሙያ ስለመኖሩ ቅሬታውን ካቀረበ በኃላ የህግ ባለሙያ ስለመሆኑ መረጃ ማግኘት እንዳልቻለ ተናግሯል።

የኬንያ የሕግ ማኅበርን የውስጥ ምርመራን ተከትሎ፣ በሌላ ጠበቃ ስም በመግባት ብሪያን ምዌንዳ ንጃጊ ስርዓቱን ጥሶ መቀላቀሉን ይፋ አድርጓል።ማህበሩ ሰነዶችን ካሰባሰበ በኃላ በቁጥጥር ስር እንዲውል አድርጓል።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *