መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 6፤2016 – በድንኳን ዉስጥ የአንበሳ የከተማ አዉቶብስ ተሽከርካሪ ካደረሰዉ አደጋ በኋላ ተቋሙ ቸል ብሎናል ሲሉ ተጎጂዎች ተናገሩ

???????? ተቋሙ በበኩሉ ሀዘንተኞችን አጽናንቻለሁ ፤ የካሳ ክፍያ ሂደቶችንም እጀምራለሁ ብሏል

መስከረም 26 ቀን በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 አለምጸሀይ ድልድይ በተሰኘዉ አካባቢ ያገጠመን ሀዘን ተከትሎ በድንኳን በነበሩ ሀዘንተኞች ላይ ንብረትነቱ የአንበሳ ከተማ አዉቶብስ የሆነ ተሽከርካሪ የህዝብ ማመላለሻ አደጋ አድርሶ እንደነበር ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን መዘገቡ ይታወሳል።

በአደጋዉ ባለትዳሮችን ጨምሮ በወቅቱ ባለቤቷን ያጣች ግለሰብ እናቷን መነጠቋ ታዉቋል። የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉንም መዘገባችን አይዘነጋም።

አደጋዉ ካጋጠመ በኋላ ግን ሀዘንተኞች አንበሳ የከተማ አዉቶብስ አገልግሎት ድርጅት እንዳላጽናናቸዉ ተጎጂዎችን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን በጎበኘበት ቅኝት ተናግረዋል። ቅሬታቸዉን ያቀረቡ ተጎጂዎችም በአደጋዉ ጉዳት ለደረባቸዉ ሰዎች የህክምና ወጪዎችን ተቋሙ እሸፈነ አለመሆኑንም ገልጸዋል።

ጣቢያችን የአንበሳ የከተማ አዉቶብስ አገልግሎት ድርጅት የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ፍሰሃን ያነጋገረ ሲሆን ተቋማቸዉ በስራ አስኪያጁ አማካኝነት ሀዘንተኞችን ማጽናናቱን ተናግረዋል።

አንበሳ የከተማ አዉቶብስ አገልግሎት ድርጅትም የካሳ ክፍያ ሂደቱን ለማስጀመር አደጋዉ ያጋጠመበትን የምርመራ ሪፖርት ከፖሊስ እየጠበቀ ነዉ ብለዋል። ሪፖርቱን እንዳገኘም የካሳ ክፍያዉ ይፈጸማል ብለዉናል።

ሆኖም ተጎጂዎች በተቋሙ የስራ ሃላፊዎች አለመጽናናታቸዉን ጠቅሰዉ ቅሬታ ፈጥሮብናል ብለዋል።

በወላይታ ሶዶ የህግ ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት አቶ አበባየሁ ጌታ መሰል አደጋዎች አደጋዎች ሲከሰቱ ከአደጋ አድራሹ ግለሰብ ባለፈ ተቋማት ተጎጂዎችን ከማጽናናት አንስቶ ተገቢዉን የካሳ ክፍያ የመፈጸም ግዴታ ያለባቸዉ መሆኑን ጨምረዉ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *