መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 7፤2016 –ከሰማንያ አመቷ አዛውንት 10 ሺህ ብር የሰረቁ ሁለት ሴቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በካፋ ዞን በጊምቦ ወረዳ ዑፋ ከተማ ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፋዱ 5 ሰዓት የግል ተበዳይ ከባንክ 10 ሺህ ብር በማውጣት በባለሶስት እግር ባጃጅ ተሳፍረው ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲሄዱ  ከአዛውንቷ ዘንቢል ውስጥ እስከ ቦርሳው ሰርቀው በመውድ ባጃጁን አስቁመው መውራዳቸው ተገልጿል ።

የ80 አመቷ አዛውንት ገንዘባቸውን ካስቀመጡበት በማጣታቸው ባሰሙት የድረሱልኝ ጩኸት የአከባቢው ህብረተሰብ እና ፖሊስ ደርሰው ሁለቱ ሴቶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ  በተደረገ ፍተሻ የሰረቁት 10 ሺህ ብር ፣ የግለሰቧ የእጅ ቦርሳ እና መታወቂያ የተገኘ ሲሆን ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል ተብሏል ፡፡

በአበረ ስሜነህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *