መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 8፤2016 – የጋቦን መሪ በፕሬዝዳንትነት የሚሰጠኝ ደሞዝ ይቅርብኝ ሲሉ ተናገሩ

የጋቦን ወታደራዊ መሪ ጄኔራል ብሪስ ኦሊጊ ንጉሜ እንደ ፕሬዝዳንትነት የሚሰጣቸውን ደመወዝ እንደማይቀበሉ እና የሪፐብሊካኑ የጥበቃ አዛዥነታቸው የሚያገኙትን ደመወዝ ብቻ እንደሚቀበሉ ተናግረዋል ።

በነሀሴ ወር የፕሬዝዳንት አሊ ቦንጎ ከስልጣን መወገዱን ተከትሎ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ሆነው መሾማቻው ይታወሳል። የወታደራዊው መንግስት ቃል አቀባይ እንደተናገሩት ጄኔራል ንጉዌማ ደመወዛቸውን ላለመቀበል የወሰኑት የጋቦናውያንን ማህበራዊ፣  ድንገተኛ አደጋዎች እና ዜጎች ከእኛ የሚጠበቁት በርካያ ነገሮችን ስላሉ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ቃል አቀባዩ ኮለኔል ኡልሪክ ማንፉምቢ እንዳሉት ያለፈው እያንዳንዱ ቀን የሀገሪቱን አጠቃላይ መበላሸት እና በተለይም የመንግስት የፋይናንስ ሁኔታን የበለጠ ህዝቡ እንዲያውቅ ያስችለዋል። ከስልጣን የተወገዱት የፕሬዚዳንት ቦንጎ የ14 አመታት አገዛዝ በሙስና እና በሌሎች የፋይናንስ ቅሌቶች ክስ የሚቀርብበት የነበረ ሲሆን የወታደራዊው መንግስት የሀገሪቱ ፋይናንስ  የወንጀል ሰለባ ነበር ሲል ተናግሯል። ጄኔራል ንጉሜ በፕሬዝዳንትነት የሚያገኙትን ደመውዝ ከመተው በተጨማሪ የሕግ አውጭዎችን አበል ለመቀነስ፣ በፖለቲካ ሰበብ ፈሰስ የሚደረገውን ገንዘብ ለማስቀረ እንዲሁም በስብሰባ ላይ  የሚወጣውን አበል በማስቀረት የመንግስትን ወጪ ለመቀነስ ወስነዋል።

ፕሬዚዳንቱ ይህ ውሳኔ የመንግስት ሀብት ያጠናክራል ሲሉ አክለዋል። እርምጃው የጋቦን ህዝብ በሀገሪቱ አመራር ላይ ያለውን እምነት ለመመለስ እንደ ሙከራ ተደርጎ ተወስዷል።

በቤዛዊት አራጌ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *