የቱርክ ኩባንያ ካርፓወርሺፕ 17 ሚሊዮን ዶላር ባልተከፈለው ዕዳ ምክንያት የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦቱን ካቋረጠ በኋላ የጊኒ ቢሳው ዋና ከተማ ከትላብት ማክሰኞ ጀምሮ ጨለማ ውስጥ ትገኛለች።
የጊኒ ቢሳው ከፍተኛ ባለስልጣን ሱሌይማኔ ሰኢዲ በጊኒ ቢሳው ኤሌክትሪክ እና ውሃ ኩባንያ 15 ሚሊዮን ዶላር ውዝፍ ዕዳ ለመክፈል ዝግጅት መደረጉን ገልጸው ችግሩ በ15 ቀናት ውስጥ እንደሚፈታ ቃል ገብተዋል።በዓለም ላይ ካሉ ትላልቅ የኃይል ማመንጫዎች አንዱ እና የካራዲኒዝ ኢነርጂ ግሩፕ አካል የሆነው ካርፓወርሺፕ እ.ኤ.አ. በ 2019 ውል ከተፈራረመ በኋላ 100 በመቶ የጊኒ ቢሳውን የኤሌክትሪክ ፍላጎቶችን እያቀረበ መሆኑን በድረ-ገጹ አስታውቋል።
ሴኢዲ በሰጡት በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ “ካርፓወር የኋላ ኋላ ችግር እንዳይፈጠር ከመንግስት ጋር እንደገና ለመደራደር ተስማምቷል” ብለዋል ። የካርፓወርሺፕ ቃል አቀባይ በጊኒ ቢሳው ስላለው ሁኔታ በሰጡት መግለጫ፡ እንደ አለመታደል ሆኖ፣ ለረጅም ጊዜ ያለክፍያ ብንሰራም የእኛ የኃይል ማመንጫ አሁን ላይ ሥራውን ከዚህ በላይ መቀጠል አልቻለም ብለዋል።
ይህንን ችግር ለመፍታት ከባለስልጣናት ጋር ሌት ተቀን እየሰራን ነው እናም በተቻለ ፍጥነት የኤሌክትሪክ ኃይል ለመመለስ አላማ አለን ሲሉ ገልፀዋል። ዕዳው አሁን ያሉት ባለስልጣናት የሚመለከት ባይሆንም ነገር ግን እልባት ለመስጠት ወስነዋል ብለዋል። ባንኩ የዕዳውን የተወሰነ ክፍል የማስተላለፍ ሂደቱን እንዲያጠናቅቅ እየጠበቅን ነው ሲሉ አክለዋል።
በመስከረም ወር ካርፓወርሺፕ ወደ 40 ሚሊዮን ዶላር ባልተከፈለ ዕዳ ምክንያት የኤሌክትሪክ አቅርቦቱን በሴራሊዮን ዋና ከተማ ፍሪታውን አቋርጧል።
በበረከት ሞገስ