መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 8፤2016 – 11 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረው ባጃጅ ከፖሊስ ተሽከርካሪ ጋር ተጋጭቶ በ8 ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ

አደጋዉ የደረሰዉ በምዕራብ ኦሞ ዞን በመኤንት ሻሻ ወረዳ ባሲ ቁጥር 5 ተብሎ በሚጠራ መንደር ውስጥ  ባለሶስት እግር ባጃጅ  ከፖሊስ ተሽከርካሪ ጋር ተጋጭቶ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የዞኑ ፖሊስ ገልጿል።

የዞኑ ፖሊስ የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር አስተባባሪ ምክትል ኢንስፔክተር ጎቹ  ቦቹባብ ለብስራት ሬድዮ  እና ቴሌቭዥን እንደገለፁት ጥቅምት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:30 በደረሰ አደጋ  ከአቅም በላይ በባጃጅ ላይ 11 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ ከነበረዉ ሰዎች መካከል  በ5 ሰዎች ላይ ከባድ ጎዳት የደረሰ ሲሆን በሶስት ሰዎች ላይ ቀላል ጎዳት ደርሷል።እንዲሁም  በንብረት ላይ ግምት ያልወጣለት ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።

እንደ ኃላፊዉ ገለፃ የፖሊስ መኪና በፍርድ ቤት ወሳኔ ያገኙትን የህግ ታራሚዎችን ወደ ማረሚያ ተቋም ለማድረስ የቀኝ መስመር ይዞ እየተጓዘ ባለበት ነው ባጃጁን የገጨው።

የባጀጅ አሽከርከሪዉ ከአቅም በላይ  ሰዎችን ጭኖ  የራሱን መስመር በመተው እና  በፍጥነት በመጓዝ  መስመሩን ይዞ ይጓዝ ከነበረ ተሽከርካሪ ጋር ተጋጭቶ በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ጨምረው ለጣቢያችን ገልፀዋል።

በምህረት ታደሰ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *