መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 12፤2016-የእስራኤል የጸጥታ ሚኒስትር በጋዛ ሙሉ እርዳታ የሚገባው የታገቱት በሙሉ ሲለቀቁ ነው ሲሉ መናገራቸው ትችት አስነሳ

የእስራኤል የቀኝ አክራሪ የጸጥታ ሚኒስትር ኢታማር ቤን-ጊቪር ሃማስ በእጃቸው ያሉትን እስረኞች በሙሉ ለመልቀቅ ካልተስማማ በስተቀር ለጋዛ “ቀጣይነት ያለው እርዳታ” ዋስትና ሊኖር አይገባም ብለዋል። ቤን-ጊቪር በኤክስ ላይ ይህንኑ መግለጫ የሰጡት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 14 ሰብዓዊ ርዳታዎችን የጫኑ የጭነት ተሽከርካሪዎች ሁለተኛ ዙር እሁድ እለት ወደ ጋዛ እንዲገባ መፍቀዱን ተከትሎ ነው።

“ለጋዛ ቀጣይነት ያለው ዕርዳታ” የሚኖረው የታፈኑ ወገኖቻችንን መፈታትን ያላካተተ ማንኛውም ስምምነት በእኛ ዘንድ ተቀባይነት የለውም ብለዋል። “የታገቱት ሁሉ ሲፈቱ ሰብአዊነት ብቻ” ይኖራል ሲሉ አክለዋል። ከግጭቱ በፊት በየቀኑ ወደ 500 የሚጠጉ የእርዳታ መኪኖች ጋዛ ይገባሉ ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ ያሳያል።

ሃማስ ወደ 200 የሚጠጉ ሰዎችን አሁንም ታግተው ይገኛሉ።ግጭቱ ከተቀሰቀሰ ጊዜ አንስቶ በጋዛ 4 ሺ 6 መቶ 51 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የግዛቱ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በሃማስ ቁጥጥር ስር የሚገኘው ሚኒስቴሩ ባወጠው መግለጫ ከተገደሉት ሰዎች መካከል 1 ሺ 8 መቶ 73ቱ  ህጻናት ሲሆኑ 1ሺ 1 መቶ 1ዱ ደግሞ ሴቶች ናቸው ብለዋል።ከጠቅላላው የሟቾች ቁጥር 839 በደቡባዊ ጋዛ የተገደሉ ሲሆን ከሰሜን አካባቢዎች ሰዎች እንዲሸሹ ቢነገራቸውም በደቡባዊ አካባቢ የሰዎች ህይወት አልፏል።

በሌላ በኩል የእስራኤል ተዋጊ አውሮፕላኖች በሊባኖስ ውስጥ ሁለት የሂዝቦላህ ህዋሶችን ዛሬ ማለዳ መምታቱን የሀገሪቱ ጦር አስታውቋል።በጋዛ ግጭት ወቅት በሁለቱ ሀገራት የጋራ ድንበር ላይ ተከታታይ የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል።አንደኛው ክፍል የሚገኘው በእስራኤል ድንበር ከተማ ማታት አቅራቢያ ሲሆን ሌላኛው ክፍል ደግሞ አወዛጋቢ በሆነው የሼባ እርሻዎች ክልል ውስጥ ይገኛል። ሁለቱም ሴሎች የተመቱት ፀረ ታንክ ሚሳኤሎችን እና ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ለማስወንጨፍ ከመጀመራቸው በፊት የተመቱ ናቸው ተብሏል።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *