መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 13፤2016 –ማክሮን ከኔታንያሁ ጋር ለመምከር እስራኤል ገቡ

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በእስራኤል ቤን ጉሪዮን አየር ማረፊያ ተገኝተው ዛሬ ረፋድ ላይ በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር መክረዋል። የጉብኝቱ አላማ ፈረንሣይ ከእስራኤል ጋር ያላትን አጋርነት ለማሳየት፣በሀማስ ቁጥጥር ስር ያሉ ታጋቾችን ለማስፈታት ለመርዳት እና አሁን ያለው ግጭት እንዳይባባስ ለማድረግ መሆኑን የፕሬዝዳንቱ አማካሪዎች ለሮይተርስ ተናግረዋል።
ማክሮን በጉብኝታቸው የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ እና የመሃል ፖለቲካ መሪዎቹ ቤኒ ጋንትዝ እና ያየር ላፒድን ከተቃዋሚዎች ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ከሃሙስ እስከ እሁድ ዋሽንግተንን እንደሚጎበኙ እና ከአሜሪካ አቻቸው አንቶኒ ብሊንከን እንዲሁም ከብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን እንደሚገናኙ የአሜሪካ ባለስልጣናት ገልፀዋል።

ባለሥልጣናቱ በጉብኝቱ ወቅት በእስራኤል እና በዩክሬን ውስጥ ባሉ “ሁኔታዎች” ላይ ቤጂንግን “ይበልጥ ገንቢ አቀራረብን” እንደሚገፋ ተናግረዋል። ነገር ግን ዋንግ ከፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጋር እንደሚመክሩ እስካሁን በግልፅ የታወቀ ነገር የለም።ከጉዞው በፊት ዋንግ ከእስራኤልን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤሊ ኮሄን ጋር በስልክ ውይይት አድርገዋል።

የአሁኑን ግጭት “በጦርነት እና በሰላም መካከል ያለ ዋና ምርጫ” በማለት ገልፀዋል ። ሁሉም ሀገራት እራሳቸውን የመከላከል መብት አላቸው ነገር ግን አለም አቀፍ የሰብአዊ ህግጋትን ማክበር እና የሲቪሎችን ደህንነት መጠበቅ አለባቸው ሲሉ ዋንግ አክለው ተናግረዋል።ዋንግ የፍልስጤም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪያድ ማልኪን አነጋግረው “በተቻለ ፍጥነት ውጤታማ የሆነ ዓለም አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ” እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል። ቻይና የሁለት ሀገራት መፍትሄ እንደምትደግፍ ገልፀዋል ። 

በአበረ ስሜነህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *