መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 13፤2016-ከሀማስ እገታ ነፃ የወጡት የ85 ዓመቷ አዛውንት የሃማስ ታጣቂዎች እንክብካቤ እንዳደረጉላቸው ተናገሩ

በገሃነም ውስጥ ገብቼ ነበር ያሉት የ85 ዓመቷ አዛውንት ዮቼቭድ ሊፍሽቺትዝ ከሁለት ሳምንታት እገታ በኋላ በሃማስ ከእገታ በትላንትናው እለት ተለቀዋል።

የሰላም ታጋይ እንደሆኑ የሚናገርላቸው አዛውንቷ ሊፍሽቺትስ እና ባለቤታቸው በሃማስ ታጣቂዎች በሞተር ሳይክሎች ታግተው “የሸረሪት ድር” ውስጥ በጋዛ ዋሻ መወሰዳቸውን ተናግረዋል። በጉዞ ላይ እያለው በዱላ ተመትቻለው ያሉ ሲሆን ነገር ግን አብዛኞዎቹ ታጋቾች “በጥሩ ሁኔታ እንደተያዙ’  ተናግረዋል።

ሰኞ አመሻሽ ላይ ኑሪት ኩፐር ከተባሉ ሎብ 79 ዓመት እድሜ ካላቸው ሴት ጋር ተፈተዋል። አዛውንቷ ከእገታ ሲለቀቁና የሃማስ ታጣቂ አባል እጅ ሲጨብጡ የሚያሳይ ምስል የተጋራ ሲሆን በአለም አቀፍ ቀይ መስቀል አምቡላንስ ተሽከርካሪው ወደ እስራኤል ተወስደዋል። ከሀማስ ታጣቂ ጋር ሲለያዩ ሻሎም የሚል ቃልን የተናገሩ ሲሆን በዕብራይስጥ ቋንቋ ሰላም ማለት ነው።

ወይዘሮ ሊፍሺትዝ ከባለቤታቻው ኦዴድ ጋር በደቡባዊ እስራኤል ኒር ኦዝ ኪቡትዝ  አካባቢ ሀማስ ጥቃት በከፈተበት እለት ታግተዋል። ባለቤታቸው ግን እስካሁን አልተፈታም። አዛውንቷ ከእገታ ከተለቀቁ ከጥቂት ሰአታት በኋላ በቴል አቪቭ ከሚገኝ ሆስፒታል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ወደ ጋዛ በሄድንበት ወቅት በዱላ ተመቼ ጉዳት ደርሶብኛል የመተንፈስ ችግር አጋጥሞኛል ብለዋል።

የእናቷን መከራ ለጋዜጠኞች በመንገር የረዳችው ልጇ ሻሮን ሊፍሺትዝ የ85 ዓመቷ አዛውንት ጥቂት ኪሎ ሜትሮች በእግር ለመጓዝ መገደዳቸውን ተናግራለች። ሻሮን እናቷ “የሸረሪት ድር በሚመስሉ በጋዛ ስር ወደሚገኝ ግዙፍ ዋሻ መረብ” መወሰዳቸውን አክላለች። ወይዘሮ ሊፍሽቺትስ ከታጣቂው ጋር ለምን እንደተጨባበጡ በጋዜጠኛ ሲጠይቋት ታጋቾቹ በጥሩ ሁኔታ እንዳስተናገዷቸው እና ቀሪዎቹ ታጋቾች በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል 

ሊፍሺትዝ እና የ83 ዓመቱ ባለቤታቸው የታመሙ ሰዎችን ከጋዛ ወደ እስራኤል ሆስፒታሎች በማጓጓዝ የረዱ የሰላም ተሟጋቾች እንደነበሩ ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል። የኑሪት ኩፐር ባለቤትም አሁንም በሃማስ ታስሮ ይገኛል።

ሁለት አሜሪካ-እስራኤላውያን እናትና ሴት ልጃቸው ጁዲት እና ናታሊ ራናን አርብ ዕለት ከታገቱበት መለቀቃቸው ይታወሳል። እስራኤል አሁንም ከ200 በላይ ሰዎች ታግተው እንደሚገኙ ተናግራለች።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *