
ቦቢ የተሰኘዉና በፖርቱጋል ይኖር የነበረዉ የአለም አዛዉንቱ ዉሻ ህይወቱ ማለፉን አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል።
ዉሻዉ በአለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ረጅም አመታትን የኖረዉ ዉሻ በሚል ተመዝግቦ ነበር። በፖርቱጋል ገጠራማ ቦታ ይኖር የነበረዉ ዉሻ 31 አመት ከ 165 ቀናት በዚች ምድር ላይ መቆየቱ ተነግሯል።
ቦቢ በ 1939 ህይወቱ ካለፈዉና የአዉስራሊያ ዘር ካለዉ ብሉይ ከተሰኘዉና 29 አመታትን ከኖረዉ ዉሻ ነበር ሪከርዱን የተቀበለዉ። የዉሻዉ ከባለቤቱ በ 8 አመታት ብቻ የሚያንስ ሲሆን ረጅም አመታትን የመኖሩ ሚስጥር በጥሩ መልኩ ስለሚመግቡት ፣ ንጹህ አየር እና ፍቅር ስለሚሰጡት እንደሆነ አሳዳጊዎቹ ተናግረዋል።
የጊነስ ድንቃድ መዝገብ በዉሻዉ መሞት የተሰማዉን ሀዘን የገለጸ ሲሆን በዉሾች የእድሜ ዘመን አቆጣጠር 217 አመት ኖሯል ብሏል። ዉሾች በአማካይ ከ 10 እስከ 13 አመታት የህወት ዘመን ይኖረዋል ተብሎ የሚገመት ሲሆን የአለም አዛዉንቱ ዉሻ በ 31 አመቱ ህይወቱ አልፏል ተብሏል።
በኤደን ሽመልስ