መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 14፤2016-ኢትዮጵያ በአንድ ዓመት ውስጥ ከ1መቶ ሺህ ቶን በላይ የዶሮ ስጋ ማምረቷ ተነገረ

በባለፈው የ2015  በጀት አመት ኢትዮጵያ 1መቶ 12 ሺህ ቶን የዶሮ ስጋ ማምረት መቻሉን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በሚኒስቴሩ የዶሮ ሀብት ልማት ዴስክ ኃላፊ አቶ ዮናስ ዘውዴ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ከሆነ እንደ ሀገር የዶሮ ስጋ ምርቱ ጥሩ ሊባል የሚችል ቢሆንም በሚፈለገው ልክ ዜጎች የዶሮ ስጋን እየተመገቡ አይደለም ብለዋል።

የዶሮ ስጋ ያለው የምግብ ይዘት የተሻለ በመሆኑ የመቀንጨር ችግርን ለመፍታትና ጤናማ ዜጋን ለመፍጠር ሚናው የላቀ እንደሆነ ቢገለፅም የዶሮ ስጋን የሚመገቡ ዜጎች ቁጥር ግን ዝቅተኛ ነው ተብሏል።ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህን ችግር ለመፍታት ህብረተሰቡ የዶሮ ስጋን የመመገብ ባህሉን እንዲያዳብር የተለያዩ የግንዛቤ ከመፍጠር በተጨማሪ ዋንኛው እንቅፋት የሆነውም የዶሮ ስጋ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተለያዮ ስራዎች  ለመስራት ማቀዱን ተናግረዋል።

በቀጣይ በባህላዊ መንገድ የሚከናወኑ የዶሮ እርባታዎችን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራል ሲሉ አቶ ዮናታን አክለዋል።በተጨማሪም ከ38 እስከ 45 ቀናት ባሉት ጊዜያት ለስጋ  ብቻ እንዲሆኑ የተለዩ ዶሮዎች ምርት እንዲሰጡ በማድረግ የዶሮ ስጋ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ መታቀዱን አክለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *