መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 14፤2016-የበጂንካ ከተማ ወደ ኬኒያ ሊሻገር የነበረ የካናቢስ አደንዛዥ እፅ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተነገረ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኣሪ ዞን በጂንካ ከተማ ስድስት ኩርት ላስቲክ የካናቢስ አደንዛዥ እፅ ከሁለት ግለሰቦች ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉ ተነግሯል 

አደንዛዥ እፁን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከጂንካ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት እንዲሁም ከዞኑ ፖሊስ መምሪያ መረጃ ኢንተለጀንስ ስውር ክትትል ዘርፍ  ጋር በመሆን እንደተያዘ ተገልጿል ።

ብዛቱ 6 ኩርቱ ላስቲክ የሆነው የካናቢስ እፅ ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን የጂንካ ከተማ ኮሚኒኬሽን ባለሙያ የሆኑት አ/ቶ የሱፍ አህመድ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

በተጨማሪም ባጃጅ እና አንድ ሞተር ሳይክል በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ፖሊስ በተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ ተገልጿል ። ከአሁን ቀደም በእርሻ ማሳ ተዘርቶ ለአገልግሎት የደረሰ የካናቢስ እፅ ተክል እንዲወገድ መደረጉን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥ መዘገቡ ይታወሳል ።

በአበረ ስሜነህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *