መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 15፤2016 – በአሜሪካ ሜይን ግዛት በጅምላ በተከፈተ ተኩስ ቢያንስ 22 ሰዎች ተገደሉ

በዩናይትድ ስቴትስ ሰሜናዊ ምስራቅ ሜይን ግዛት ውስጥ አንድ ታጣቂ በከፈተው ተኩስ ቢያንስ 22 ሰዎች ሲግደሉ ከ50 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል ተብሏል። በጥቃቱ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሁለት የሉዊስተን ከተማ የህግ አስከባሪ ባለስልጣናት ለአሶሺየትድ ፕሬስ የዜና ወኪል ተናግረዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ መገናኛ ብዙሃን የሆነው ኤንቢሲ ኒውስ በበኩሉ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉትን የሉዊስተን የሕግ አስከባሪ ባለሥልጣንን ጠቅሶ በጥቃቱ ቢያንስ 22 ሰዎች መሞታቸውንና 60 የሚደርሱ ቆስለዋል ሲል ዘግቧል። በመቶዎች የሚቆጠሩ የግዛቱ እና የአካባቢው ፖሊሶች  ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየፈለጉ ይገኛል ተብሏል። ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉ እና እንደተጎዱ ግን አልገለጹም።

39,000 ያህል ሰዎች በሉዊስተን ይኖራሉ።የሉዊስተን ፖሊስ ዲፓርትመንት ሮበርት ካርድ የተባለ ሰው ፎቶ በፌስቡክ ገጹ ላይ በማውጣት አፋልጉኝ ብሏል። “ካርድ እንደታጠቀ እና አደገኛ እንዳሆነ በመግለፅ” ህብረተሰቡ ወደ እርሱ እንዳይቀርቡ ወይም እንዳይገናኝ አሳስበዋል። ታጣቂው ኢላማ ያደረገው የመጠጥ ቤት ፣ የቦውሊንግ ስፍራ እና የዋልማርት ማከፋፈያ ማዕከል ነው ሲል ሰን ጆርናል ጋዜጣ ዘግቧል።

የግዛቱ የፖሊስ ባወጣው መረጃ ካርድ በሜይን በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሃይል ማሰልጠኛ ማዕከል የጦር መሳሪያ አስተማሪነት የሰለጠነ ቢሆንም ድምጽ የመስማትን ጨምሮ የአእምሮ ጤና ችግር እንደነበረበት ተናግሯል። የ 40 አመቱ ጎልማሳ በበጋው ወቅት በአእምሮ ጤና ተቋም ውስጥ ለሁለት ሳምንታት አሳልፏል።ቡናማ ሸሚዝ የለበሰ እና ጠቆር ያለ የውጊያ ሱሪ ማድረጉን እንዲሁም ጠመንጃ ትከሻው ላይ አድርጎ ያለበት ሁለት ፎቶግራፎች ተጋርቷል።

ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ስለ ጥቃቱ ገለጻ የተሰጣቸው ሲሆን ከሜይን ግዛት ገዥ ጃኔት ሚልስ፣ ሴናተሮች አንገስ ኪንግ እና ሱዛን ኮሊንስ እና ኮንግረስማን ጃሬድ ጎልደን ጋር በተናጥል በስልክ ተነጋግረዋል። ጥቃቱን ተከትሎ ሙሉ የፌደራል ድጋፍ እንደሚደረግ ዋይት ሀውስ አስታውቋል። የ22ቱ ሰዎች ሞት ከተረጋገጠ የሉዊስተን ጥቃት ቢያንስ በ2019 አንድ ታጣቂ በኤል ፓሶ ዋልማርት ሸማቾች ላይ በኤኬ-47 ሽጉጥ ተኩስ ከፍቶ 23 ሰዎሽን ገደለ ከተባለበት ጥቃት በኋላ በአሜሪካ ውስጥ በጅምላ ከፍተኛው የተኩስ ግድያ ይሆናል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *