መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 15፤2016 – ከኔታናሁ ጋር በመጨባበጤ ተፀፅቻለሁ ሲሉ ኤርዶጋን ተናገሩ

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን እስራኤል በጋዛ ላይ ለምታደርሰው የቦምብ ጥቃት የምዕራባውያን መንግስታት የሰጡትን ምላሽ አሳፋሪ ነው ሲሉ ገልፀዋል። ምዕራባውያን እርምጃ እየወሰዱ አይደለም ምክንያቱም የፈሰሰው ደም በመካከለኛው ምስራቅ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ ምን ሆነ?” ብሎ ማን ጠየቀ ሲሉ ከሰዋል። ምእራባውያን አላማቸውን ካላስፈፀመ አይመለከቱትም ሲሉ አክለዋል ። ለምን ከተባለ ደግሞ ምክንያቱ የሚፈሰው ደም የመካከለኛው ምስራቅ ደም ነው ብለዋል። በትናንትናው እለት ኤርዶጋን ወደ እስራኤል ሊያደርጉት የነበረውን ጉዞ የሰረዙ ሲሆን ባለፈው ወር በኒውዮርክ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር በመጨባበጤ ተጸጽቻለሁ ብለዋል።

የእስራኤልን የአየር ድብደባ “የበቀል ጦርነት” ሲሉ ገልፀውታል። በሄግ በሚገኘው አለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በኔዘርላንድስ ንግግር ያደረጉት ሪያድ አል ማሊኪ የቦምብ ጥቃቱ ካለፉት የእስራኤል ጥቃቶች የከፋ መሆኑን ተናግረው የተኩስ አቁም እንዲደረስ ጠይቀዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *