መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 15፤2016 – የኬንያ የፓርላማ አባል የፍልስጤም ስካርፍ በመልበሳቸው እንዲያወልቁ ታዘዙ

አንድ የኬንያ የፓርላማ አባል በትላንትናው እለት በፓርላማ ውሎ ላይ ለብሰው የመጡትን የፍልስጤም ባህላዊ ስካርፍ እንዲያወልቁ ታዝዟል። ፋራህ ማሊም በእስራኤል እና በፍልስጤሙ ቡድን ሃማስ መካከል በቀጠለው ግጭት በጋዛ ሉሚገኙ ፍልስጤማውያን አጋርነታቸውን ለማሳየት ስካርፍ ለብሰው እንደነበር ተነግሯል።

ለፍልስጤም “በኬንያ ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው ድጋፍ ያስፈልጋታል” ሲሉ ተናግረዋል።ነገር ግን የብሔራዊ ምክር ቤቱ አፈ-ጉባዔ ርምጃው የፓርላማውን ህግ የሚጥስ ነው በማለት የፓርላማ አባሉን ስካርፍ እንዲያወልቁ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።

የፓርላማ አባላትም የህግ አውጭውን የምክር ቤቱን ህግጋት “ያላከበረ” ሲሉ አውግዘዋል። የኬንያ ፖሊስ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ በተካሄደው የፍልስጤም ድጋፍ ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል ያላቸውን ሶስት ሰዎች ለአጭር ጊዜ ካሰራቸው ከጥቂት ቀናት በኋላ መልቀቁ ይታወሳል። ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ መንግስታቸው በቀጠለው ግጭት ለእስራኤል ሙሉ ድጋፍ እንደሚሰጥ መናገራቸው አይዘነጋም።

በቤዛዊት አራጌ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *