????????????????የሐማስ የታጠቂ ክንፍ ቡድን አል-ቃሳም ብርጌድ በቴሌግራም የመልእክት ማጋሪያ ላይ ባሰፈረው መልዕክት”በሲቪሎች ላይ ለተፈፀመው የጽዮናውያን ጭፍጨፋ የአፀፋ ምላሽ” እንዲሁን ወደ ቴል አቪቭ ሮኬቶችን መተኮሱን ተናግሯል።
????????????????????????ፔንታጎን 900 ተጨማሪ የአሜሪካ ወታደሮች ወደ መካከለኛው ምስራቅ እያመሩ ቢሆንም ወደ እስራኤል አይሄዱም ብሏል። የፔንታጎን ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጄኔራል ፓትሪክ ራይደር በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት ወታደሮቹ “ሰፋ ያለ ግጭትን ለመግታት እና የጥበቃ አቅማችንን ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት” ወደ መካከለኛው ምስራቅ እያመሩ ነው ብለዋል።
????????????????በጋዛ በእስራኤል የአየር ጥቃት የተነሳ የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር 7,028 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል። በተገለፀው አሃዝ መሰረት ከሟቾቹ መካከል 2,913 ያህሉ ህጻናት መሆናቸው ተመላክቷል።
????????????????በጋዛ ወደ 200 ሺ የሚጠጉ መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ እና በከፊል መውደማቸውንም የፍልስጤም ባለስልጣናት ተናግረዋል።
????????????????????????የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በበኩላቸው እስራኤል በጋዛ ላይ ያደረሰችው ጥቃት ራስን የመከላከል ጣሪያ አልፏል ወደ ግልፅ ጭቆና፣ ጭካኔ፣ እልቂት እና አረመኔነት ተለውጧል ሲሉ ተናግረዋል።
????????????????????????እስራኤል በጋዛ ላይ ያደረሰችውን ጥቃት በመቃወም በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢራቃውያን ነዳጅ ጫኝ መኪኖችን ወደ ዮርዳኖስ እንዳያቋርጡ እየከለከሉ ይገኛል።የኢራቅ የነዳጅ ዘይት ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት ወዳላቸው ሀገራት እንዲላክ አንፈቅድም ሲሉ ሰልፈኞች ተደምጠዋል።
????????????????የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር የናታንያሁ የጦር ካቢኔን የተቀላቀሉት የቀድሞ ጄኔራል ቤኒ ጋንትዝ ከሃማስ በተጨማሪ የእስራኤል ጠላቶች ሊወድሙ እንደሚገባ ጥሪ አስተላልፈዋል።
????????????????የፍልስጤም ቀይ ጨረቃ ማህበር በራፋ ድንበር መሻገሪያ ላይ ከግብፅ ቀይ ጨረቃ የምግብ፣መድሀኒት እና የህክምና ቁሳቁሶችን የያዙ 12 የጭነት ተሽከርካሪ መረከቡን አስታውቋል።
በስምኦን ደረጄ