???????????????????????? የሩሲያ ዋና ከተማን ሞስኮን እየጎበኘ የሚገኘው የሃማስ ከፍተኛ ባለስልጣናት ልዑካን የተኩስ አቁም ስምምነት እስካልተገኘ ድረስ ወታደራዊ ቡድኑ ታጋቾችን መልቀቅ እንደማይችል የሩሲያው ኮምመርሰንት ጋዜጣ ዘግቧል። ጋዜጣው የሀማስ አመራር የሆኑት አቡ ሀሚድን ጠቅሶ እንደዘገበው እስራኤል በጋዛ ላይ ባደረሰችው የቦምብ ጥቃት 50 ታጋቾችን መግደሏን እና ቡድኑ በተለያዩ የፍልስጤም ክፍሎች ወደ ጋዛ የተወሰዱትን ሁሉ ለማግኘት ጊዜ ያስፈልገዋል ብለዋል።
????????????????ከ100 ሺ በላይ እስራኤላውያን ሃማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት ከፈፀመበት ጊዜ አንስቶ በመንግስት ባለስልጣናት ማበረታቻ እና ስለ ሀገራቸው ደህንነት አዲስ ጥርጣሬ ስለተሰማቸው የጠመንጃ ፍቃድ ማመልከቻ ማስገባታቸው ተሰምቷል።
????????????????ማሪቭ የተሰኘ ተቋም በቅርቡ ከሕዝብ በሰበሰበው አስተያየት መሠረት ግማሽ ያህሉ እስራኤላውያን የጋዛ ሰርጥ ወረራን መንግስት እንዲያቆም ይፈልጋሉ ብሏል። ይህው መጠይቅ ከ522 እስራኤላውያን በተወሰደ የናሙና ዳሰሳ ጥናት ታውቋል።
????????????????የሀገሪቱ ጦር በአስቸኳይ ወደ መጠነ ሰፊ የመሬት ጥቃት ማደግ አለበት ወይ ተብለው ሲጠየቁ 29 በመቶው የተስማሙ ሲሆን 49 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ “መጠበቅ ይሻላል” ብለዋል። 22 በመቶው የሚሆኑት ግን ምንም ምላሽ አልሰጡም።
????????????????????????አሜሪካ በበኩሏ በሶሪያ በኢራን በሚደገፉ ስፍራዎች ላይ የምታደርገው ጥቃት ከእስራኤል እና ጋዛ ጦርነት ጋር ግንኙነት እንደሌለው በመግለጽ ጥቃት ሰንዝራለች።
????????????????????????በምስራቃዊ ሶሪያ የሚገኙ ሁለት ተቋማትን መምታቱን ገልፆ፣ የኢራን ሃይሎች እና አጋር ቡድኖች ይጠቀሙባቸው ነበር በማለት፣ ጥቃቱ ከእስራኤል ጋዛ ጦርነት ጋር አይገናኝም ስትል ገልፃለች።አሜሪካ ይህንን ትበል እንጂ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የመካከለኛው ምስራቅ ኢንስቲትዩት የመካከለኛው ምስራቅ እና የሰሜን አፍሪካ ኤክስፐርት ሀሰን ምንይምነህ ለአልጀዚራ እንደተናገሩት ሁለቱ ክስተቶች ሊነጣጠሉ አይችሉም ብለዋል።
????????????????????????ባለፈው ሳምንት በቀጠናው የሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮች ቢያንስ 16 ጊዜ ጥቃት ከተፈፀመባቸው በኋላ ዩናይትድ ስቴትስ የአፀፋ ምላሽ ሰጥታለች።
????????????????የእስራኤል ጦር ባወጣው መግለጫ ደግሞ የጥቅምት 7ቱን ጥቃት በማቀድ የረዳውን የሃማስ ከፍተኛ አዛዥ መግደሉን ይፋ አድርጓል።የመከላከያ ሃይሉ ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ በደርዘን የሚቆጠሩ የሃማስ ኢላማዎችን መምታቱን ገልጿል።
????????????????በጋዛ የሚገኙ የተባበሩት መንግስታት መጠለያዎች ሊይዟቸው ከሚችሏቸው አቅም በሦስት እጥፍ የበለጠ ደርሰዋል ሲል የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ኃላፊ በማስጠንቀቅ ዕርዳታ “በጭንቅ እየገባ ነው” ብለዋል።
????????????????????የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ በጋዛ አፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲደረስ በዛሬው እለት ድምጽ ይሰጣል። ረቂቅ የውሳኔ ሃሳቡ ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ እና የአለም አቀፍ የሰብአዊ ህግጋትን ማክበርን ይጠይቃል።
በስምኦን ደረጄ