መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 18፤2016 – በ ፍሬንድስ ተከታይ የቴሌቪዥን ድራማ የሚታወቀው ማቲዉ ፔሪ ከዚህ አለም በሞት ተለየ

በ ፍሬንድስ ተከታይ የቴሌቪዥን ድራማ አስቂኝ እና ተወዳጅ ገጸ ባህሪን ተላብሶ ሲተዉን የሚታወቀው ማቲዉ ፔሪ ከዚህ አለም በሞት መለየቱ ተዘግቧል።

ሎስ አንጀለስ ታይምስ እንደዘገበው ፔሪ ቅዳሜ ዕለት በሎስ አንጀለስ በሚገኘው መኖሪያው ውስጥ የመስጠም አደጋ በሚመስል ህይወቱ አለፈ ሲል የህግ አስከባሪ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል። የተዋናዩ ህልፈትም በፖሊስ እየመረመረ ነዉ ተብሏል።

የዋርነር ብሮስ ቴሌቪዥን የምንወደው ወዳጃችን ማቲው ፔሪ በሞት በማለፉ በጣም አዝነናል ፤ ማቲው የማይታመን ተሰጥኦ ያለው ተዋናይ እና የማይጠፋ የዋርነር ብሮስ ቴሌቭዥን ቡድን ቤተሰብ አካል ነበር ሲል ተዋናዩን ገልጾታል።

የሎስ አንጀለስ የእሳት አደጋ መከላከያ ዲፓርትመንት ቃል አቀባይ ብሪያን ሀምፍሬይ ለ ሲ ኤን ኤን እንደተናገረው የ911 ጥሪ ከቀኑ 4፡07 ላይ ደርሷቸዉ ፤ ከውሃ ዉስጥ የማዳን ድንገተኛ አደጋ ሰምተዉ ወደ ቦታዉ ማቅናታቸውን ተናግረዋል።

ፔሪ በዊልያምስታውን ማሳቹሴትስ ከተማ ከተዋናይ አባት እና ከጋዜጠኛ እናት የተወለደ ሲሆን በ 54 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

ፔሪ በ 2022 ከአንጀት ጋር በተገናኘ ባጋጠመዉ ህመም 2 በመቶ ብቻ የመዳን እድል እንዳለዉ በሀኪሞች እንደተናገረው በወቅቱ ገልጾ ነበር። ይህንንም ለመፈወስ 14 ጊዜ በሆዱ ላይ የቀዶ ጥገና ህክምና ያስፈልገዉም ነበር።

ተዋናዩ ያለበትን የአደንዛዥ እጽ ተጠቃሚነት ለማቆምም 15 ጊዜ የሱስ ማገገሚያ ዉስጥ ገብቶ እንደነበር ሲ ኤን ኤን አስነብቧል።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *