
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በሀገረ ስብከታቸው ውስጥ በተለያዩ ተግባራት ለሴቶች አመራር ቅድሚያ እንዲሰጡ ጳጳሳትን ማዘዛቸውን በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ከፍተኛ የካቶሊክ ቄስ ገልፀዋል።
ከአንድ ወር በፊት በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የብፁዕ ካርዲናልነት ማዕረግ ያገኙት የጁባ ሊቀ ጳጳስ እስጢፋኖስ አሜዩ ማርቲን ሙላ ሰኞ ማለዳ ከቫቲካን ወደ አገራቸው ተመልሰዋል። በመስከረም ወር በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ወደ ካርዲናልነት ማዕረግ ከበቁ ሦስቱ አፍሪካውያን ሊቀ ጳጳሳት መካከል አንዱ ናቸው።
ከታንዛኒያ ካርዲናል ፕሮታሴ ሩጋምዋ እና ብፁዕ ካርዲናል እስጢፋኖስ ብሪስሊን ከደቡብ አፍሪካ ማዕረጉን ማግኘታቸው ይታወሳል። በዓለም ዙሪያ ከ21 አዲስ ካርዲናሎች መካከል ናቸው።በዋና ከተማዋ ጁባ በሚገኘው የቅድስት ቴሬዛ ካቴድራል የደስታ ግብዣ ላይ ብፁዕ ካርዲናል አሜዩ እንደተናገሩት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በሲኖዶሱ ውስጥ ሴቶች እንዲሳተፉ በመጠየቃቸው ቤተክርስቲያኒቱ በስብከተ ወንጌል ውስጥ ስላላት ሚና ተወያይተዋል። “በሲኖዶሱ ውስጥ ጳጳሱ ሴቶችን እናስቀድም ብለዋል፤ ሴቶችን ካስቀደምን ይህች ቤተ ክርስቲያን በጥንካሬ ትቆማለች ሲሉ አክለዋል።
በጠቅላይ ቤተ ክህነታችን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በሁሉም የቤተክርስቲያናችን ኮሚቴዎች ውስጥ ሴቶች የሠሩትን ሥራ እናከብራለን። “ዛሬ ደቡብ ሱዳን በጦርነት ፈርሳለች፣ ቤተሰባችን በጠብ ፈርሷል፣ እናቶች ከቤት ሲወጡ ተሰብሯል፣ ኃላፊነት በጎደላቸው አባቶች ከቤት በወጡበት ሁሉም ነገር የተበላሸ ሕይወት አለን” ሲሉ ብፁዕ ካርዲናል አሜዩ ተናግረዋል።
በስምኦን ደረጄ