መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 20፤2016-የቀድሞ የጋና ሚኒስትር 40 ሺ የአሜሪካን ዶላር የገንዘብ ስጦታ በቸልተኝነት መቀበላቸውን አመኑ

አሁን ላይ ከስልጣን የተባረሩት የጋና መንግስት ሚኒስትር የ40,000 ዶላርየገንዘብ ስጦታ መቀበላቸውን አምነዋል። “የባለሀብቶችን ስሜት ላለማስቀየም” ሲሉ ድርጊቱን መፈፀማቸውን ይፋዊድ ዘገባ አመላክቷል።

ባለፈው ዓመት ህዳር ቻርልስ አዱ ቦሄን በአህጉሪቱ 500 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳለቻው ከገለጹት ባለሀብት ገንዘቡን ሲቀበሉ የሚያሳይ አንድ የምርመራ ጋዜጠኛ የምስል ዘገባ በኃላ የሚኒስትርነት ስራቸው ተባረዋል። በጋና ከሙስና እና ከሙስና ጋር የተያያዙ ተግባራትን የሚመረምረው የጋና ልዩ አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት የስድስት ወራት ምርመራ በማድረግ ሪፖርቱን ሰኞ ይፋ አድርጓል።

የሚዲያ ኩባንያ የሆነው ታይገር አይ ምስጢራዊ ቀረጻን በቀድሞ ሚኒስትር አዱ ቦሄን “ከታቀደው ኢንቨስትመንት 20 በመቶው እንዲታሰብላቸው እና ለምክትል ፕሬዚዳንቱ 200,000 ዶላር እንዲከፍሉ መጠየቁን ዘገባው ያሳያል። ምክትል ፕሬዚዳንቱ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም ይላል። ልዩ አቃቤ ህግ ኪስ አግያቤንግ እንዳሉት ቦሄን ትክክለኛ የማመዛዘን እጦት ታይቶባቸዋል ብሏል።

የገንዘብ ስጦታውን የተቀበሉት ባለሃብቱን ሼክ ላለማስከፋት ነው የሚለው አባባል አቃቤ ህግ አልተቀበለውም። በተጨማሪም የቀድሞ ሚኒስትር ምክትል ፕሬዚዳንቱን ስም በማንሳት ረገድ “በጣም ግድየለሽነት” ታይቶባቸው ነበር ብለዋል ። ምንም እንኳን እነዚህ ድምዳሜዎች አዱ ቦሄን የወሰዱት እርምጃ “በተፅዕኖ ለመገበያየት ወይም በመሸጥ ላይ ተጽዕኖ ያሳደረ” ቢሆንም በጋና ህግ የወንጀል ጥፋቶች አይደሉም እና በዚህም ምክንያት ሊከሰሱ አይችልም ሲል ደምድሟል።

በኤደን ሽመልስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *