መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 21፤2016-የጋና የእግር ኳስ ኮከብ አሳሞአ ጂያን ለቀድሞ ሚስቱ ሁለት ቤት እንዲሰጥ በፍርድ ቤት ተወሰነበት

የጋና ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀድሞ የጋና የእግር ኳስ ኮከብ ተጫዋች አሳሞአ ጂያን በእንግሊዝ የሚገኝ መኖሪያ ቤት፣ በጋና ዋና ከተማ አክራ የሚገኝ ባለ አራት መኝታ ቤት፣ የነዳጅ ማደያ እና ሁለት መኪኖች ካሳ ለቀድሞ ሚስቱ ጉፍቲ ጂያን እንዲሰጥ ፍርድ ቤቱ ዕዛዛ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ የቀድሞው የጥቁር ኮከቦች ካፒቴን የሶስት ልጆች ወላጅ አባት መሆኑን በማረጋገጥ ለቀለብ በየወሩ 25,000 የጋና ሲዲ ወይም 2,100 ዶላር እንዲከፍል ወስኗል።

የቀድሞው የእግር ኳስ ተጫዋች ባለቤቴ ታማኝ አይደለችም ብሎ ከከሰሰ በኋላ  የሶስቱ ልጆች ወላጅ አባት ላልሆን እችላለሁ ሲል ያቀረበው ክስ ለሶስት ዓመታት ያህል ቆይቷል። የዲኤንኤ ምርመራ መደረጉን ተከትሎ ሶስቱ ልጆች የእርሱ መሆናቸውን አረጋግጧል። ጥንዶቹ ቀደም ብለው ተለያይተው የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ በአሳሞአ ጂያን የቀረበለትን አቤቱታ ተከትሎ ትዳራቸውን ሰርዟል።

ፍርድ ቤቱ ወ/ሮ ጂያን ንብረቶቹን ለመግዛት ከ
ገንዘብ ነክ የሆነ መዋጮ ባታደርግም የትዳር ጓደኛዋ በእግር ኳስ ላይ ሲያተኩር ልጆቻቸውን የምትንከባከብ እሷ ብቻ ነበረች ብሏል። እ.ኤ.አ. በ 2013 ጥንዶቹን በይፋ ጋብቻ ከመመስረታቸው በፊት ፣ታሁለት ልጆች ነበሯቸው። የሀገሩ የምንግዜም ሪከርድ ጎል አስቆጣሪ የሆነው ተጫዋቹ በአለም ዋንጫ ውድድር የአፍሪካ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው። የ37 አመቱ ተጫዋች በ2006፣ 2010 እና 2014 በተጫወተበት የአለም ዋንጫ 6 የዓለም ዋንጫ ጎሎችን ጨምሮ ለጋና ብሄራዊ ቡድን 51 ጎሎችን አስቆጥሯል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *