መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 23፤2016-ሩዋንዳ ከቪዛ ነፃ ለሁሉም አፍሪካውያን ወደ ሀገሯ ጉዞ እንዲያደርጉ ፈቀደች

የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ለሁሉም አፍሪካውያን ከቪዛ ነጻ የሆነ ጉዞ አስተዋውቀዋል።ይህ ውሳኔ ሩዋንዳ አራተኛዋ ከቪዛ ነፃ ጉዞ የሚደረግባት አፍሪካዊት ሀገር ያደርጋታል።

በተጨማሪም ለእያንዳንዱ የአፍሪካ ሀገር ዜጎች እና ለበርካታ ሀገራት ዜጎች የቪዛ እገዳን አስወግደናል ሲሉ አክለዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም ስህተት አይኖርም ሲሉ አክለዋል። ማንኛውም አፍሪካዊ በፈለገ ጊዜ ወደ ሩዋንዳ በአውሮፕላን መግባት ይችላል እና ወደ ሀገራችን ለመግባት ምንም አይነት ክፍያ አይከፍልም ሲሉ ፕሬዝዳንት ካጋሜ በትላንትናው እለት ተናግረዋል።

ርምጃው በማደግ ላይ ባለው የአህጉሪቱ መካከለኛ መደብ እየተመራ ያለውን የአፍሪካ የቱሪዝም ገበያ ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ መሆኑንም አክለዋል። ሩዋንዳ የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ፣ እንደ አርሴናል እና ባየር ሙኒክ ካሉ የእግር ኳስ ክለቦች ጋር በመተባበር ሀገሪቱን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ዘመቻ ላይ ነች።

ሩዋንዳ ከሲሸልስ፣ ጋምቢያ እና ቤኒን ጋር ተቀላቅላ ለሁሉም አፍሪካውያን ዜጎች ከቪዛ ነጻ የሚገቡ የአፍሪካ ሀገራት መዳረሻ ሆናለች። በዚህ ሳምንት የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ሀገሪቱ በ2024 ለሁሉም አፍሪካዊ ጎብኝዎች የቪዛ ጥያቄን ሀገራቸው እንደምታቆም አስታውቀዋል። በርካታ የአፍሪካ ሀገራትም ከቪዛ ነፃ ለመጓዝ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን ፈፅመዋል፣ በተለይም በቅርቡ ጋና እና ደቡብ አፍሪካ እና ኡጋንዳ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተጠቃሽ ናቸው።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *