መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 23፤2016-በደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ጉዳይ በመንግስት ካቢኔ ውስጥ ከፍተኛ ውዝግብ ተነሳ

የደቡብ አፍሪካ ዋንኛ ተቃዋሚ ፓርቲ የእስራኤል እና የጋዛ ጦርነትን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት የፓርላማ አባል የሆኑ ጋሌብ ካቻሊያን ከመንግስት ካቢኔ አስወግዷል።

የዴሞክራቲክ አልያንስ (ዲኤ) አባል እና የመንግስት ልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ካቻሊያ በሁለቱ ወገኖች ግጭት ላይ የፓርቲውን አቋም ጥሰዋል ተብሏል። ፓርቲው ለእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭት ቃል አቀባይ የሾመ ሲሆን ከዚህ ውጪ አባላቱ ጉዳዩን በሚከፋፍሉ መንገድ መግለጫ ከመስጠት እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

ነገር ግን ማክሰኞ እለት ካቻሊያ በትዊተር ገፃቸው ” ዝም አልልም እስራኤል የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመች ነው።” ሲሉ ተናግረዋል። የተቃዋሚው ዲሞክራቲክ አልያንስ መሪ ጆን ስቲንሁይሰን በምክር ቤቱ አባል ንግግር የፓርላማውን ባህሪ የጣሰ “ራስ ወዳድነት እናየግል ጥቅምን ማሳደድ” ሲሉ መናገራቸውን በመንግስት ስር የሚተዳደረው ኤስኤቢሲ የዜና ድረ-ገጽ ዘግቧል።

ካቻሊያ በሰጡት መግለጫ ከዲሞክራቲክ አሊያንስ አመራርነት መባረራቸውን እና የተባረሩበት ደብዳቤ መቀበላቸውን ተናግረዋል። ሆኖም ግን ለፓርቲው ታማኝ ሆነው እንደሚቆይ ተናግረዋል ። አክለውም “በእዚህ እና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ረገጣዎችን መከታተሌን እቀጥላለሁ እናም ሁል ጊዜ እውነትን እናገራለሁ” ብለዋል ።

ካቻሊያ ከስልጣን መነሳታቸውን ተከትሎ በምትካቸው ሚሚ ጎንደዌ የፓርቲው የመንግስት የልማት ድርጅቶች ቃል አቀባይ ሆነው ይሾማሉ ተብሏል።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *