መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 23፤2016-በጃፓን “እንዴት ሹገር ዳዲን ማታለል ይቻላል” የሚል አጋዥ መፀሀፍ የሸጠችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች

ማአይ ዋታናቤ የተባለችው ግለሰብ ከሹገር ዳዲ ጋር የፍቅር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች እንዴት ማጭበርበር ይቻላል የሚል መመሪያ የያዘ መፅሃፍ በመሸጥ በቁጥጥር ስር ውላለች።

በናጎያ ጃፓን ነዋሪ የሆነችው የ25 ዓመቷ ዋታናቤ የፍቅር ጓደኛን ይማጭበርበሪያ መንገዶችን የሚያሳዩን  መመሪያዎችን ለማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮቿ በመሸጧ ተይዛለች። ካቀረበቻቸው መፅሃፎች መካከል ‘መማሪያፍ ለሹጋር ዳዲ ወዳጆ’ የሚል እና “አስማታዊ ቃላቶች ለወንዶች” በሚል ርዕስ እነዚህ መጽሃፎች ለንባብ አብቅታለች።

በዚህ መፅሃፍ ተጋላጭ የሆኑ በመካከለኛ እድሜ የሚገኙ ወንዶች ሲሆኑ በተቻለ መጠን ብዙ ገንዘብ ለማግኘት ስለሚቻልበት ዝርዝር መረጃን የያዙ ናቸው። በአወዛጋቢው የመመሪያ መጽሃፍቶቹ ውስጥ አንባቢዎች በእድሜ የገፉ የፍቅር ጓደኞቻቸው እንዲወዷቸው እና እንዲራሩላቸው ብሎም ኪሳቸውን ከፍተው በደስታ ገንዘብ እንዲሰጡ የሚያስችል ነው። ከነዚህ ስልቶች መካከል ደስተኛ ያልሆነ የልጅነት ጊዜ እንደነበራቸው እንዲነግሩ መፅሃፉ ያስተምራል።

ተጨማሪም ከተባሉ ሌሎች ስልቶች መካከል በጤና እክል ምክንያት መስራት እንዳልቻሉ እና የቤት ኪራይ ለመክፈል አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው መዋሸትን ይጨምራል።የናካ ፖሊስ ዲፓርትመንት ምንጮች እንደተናገሩት ዋታናቤ የማጭበርበሪያ መመሪያዎቿን ባለፈው አመት መሸጥ የጀመረች ሲሆን ከ10,000 ሺ የጃፓን የን ወይም ከ67 የአሜሪካን ዶላር እስከ 20,000 የን ወይም 134 የአሜሪካን ዶላር ድረስ ዋጋ በመቁረጥ ስትሸጥ ነበር።የግል ትምህርት ለሚፈልጉ ሰዎች ለተጨማሪ ክፍያ ትጠይቅ ነበር።

የጃፓን መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት ወጣቷ ከመያዟ በፊት ወደ 2,000 የሚጠጉ መጽሐፎቶችን መሸጥ ችላለች። ፖሊስ በዋታናቤ ላይ ምርመራ ማድረግ የጀመረው አንዲት 20 ዓመት ሴት የተሰጣትን መመሪያ ተከትሎ ከሁለት ወንዶች በአጠቃላይ 10.65 ሚሊዮን የን ማጭበርበሯን ተከትሎ ነው። ደራሲዋ ደንበኞቿን ማጭበርበር እንዲችሉ እንደረዳች በክሱ ላይ በዝርዝር ተቀምጧል።

በመስከረም ወር የጃፓኑ ጋዜጣ ዘ ማይኒቺ  እንደዘገበው አንድ የ50 አመት ግለሰብ 27 ሚሊየን የን በተመሳሳይ መልኩ መጭበርበሩን ለንባብ አብቅቶ ነበር።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *