መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 26፤2016 – ቻድ በእስራኤል የሚገኙትን አምባሳደሯን በማስወጣት ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነች

???? ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ያሉትን መልእክተኛዋን እንደምታስወጣ ዝታለች

ቻድ በጋዛ ሰርጥ ታይቶ በማይታወቅ አሰቃቂ ባለችው ጥቃት ላይ ምክክር ለማድረግ የእስራኤልን አምባሳደሯን እንደጠራች ተናግራለች። የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ መንግስት “የብዙ ንፁሀን ዜጎችን የሰው ህይወት መጥፋት” አውግዞ “ለፍልስጤም ጥያቄ ዘላቂ መፍትሄ የሚያመጣውን የተኩስ አቁም” ጠይቋል።

እ.ኤ.አ. በ 1972 ፣ ቻድ ፣ ከእስራኤል ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያቋረጠች ሲሆን  በ 2019 ዓመት ግንኙነቷን አድሳለች። ጦርነቱ ከተጀመረበት ከጥቅምት ወር በኋላ የእስራኤል ልዑካንዋን ስታስወጣ የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር ሆናለች። እስካሁን ቱርክ፣ቺሊ፣ባህሬን፣ሆንዱራስ፣ኮሎምቢያ እና ዮርዳኖስ አምባሳደሮቻቸውን ከእስራኤል አስወጥተዋል።

ደቡብ አፍሪካ በፍልስጤም ህዝብ ላይ  “የጅምላ ጭፍጨፋ” እየፈፀመች ነው በማለት በእስራኤል የሚገኘውን ዲፕሎማሲያዊ መልዕክተኛዋን እንደምታስወጣ ተናግራለች።ደቡብ አፍሪካውያን በጆሃንስበርግ ተቃውሟቸውን በማሰማት በጋዛ የተኩስ አቁም ጥሪ አቅርበዋል። የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ሚኒስትር ኩምቡድዞ ንትሻቭሄኒ በሰጡት መግለጫ የእስራኤል መንግስት በጋዛ ላይ ያደረሰውን የአየር ድብደባ “በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ቁጥጥር ስር ያለ የዘር ማጥፋት ወንጀል” ሲል ገልጿል።

ግጭቱ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ሌላ እልቂት ነው ሲሉ እስራኤልን አውግዘዋል፤ ደቡብ አፍሪካም እንደማትታገሰው ተናግረዋል። መንግስት በግጭቱ ላይ “አሳፋሪ አስተያየቶችን ሰጥተዋል” ያላቸውን የእስራኤል አምባሳደር ኤሊያቭ ቤሎሴርኮቭስኪ ከስልጣን እንዲነሱ ሊጠይቅ እንደሚችል ጠቁሟል።

የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶር ሁኔታው እንዳሰባቸበ ገልጸው መንግስታቸው “የእስራኤል የአፀፋ ምላሽ የጋራ ቅጣት ሆኗል” ብሎ ያምናል ብለዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ደቡብ አፍሪካውያን እስራኤል በጋዛ ላይ የሰነዘረችውን ጥቃት በመቃወም ባለፉት ሳምንታት ተቃውመዋል።

በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ በእስራኤል የሚገኘው የደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ወደ ግንኙነት ቢሮ ዝቅ ማለቱ ይታወሳል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *