በሩስያ ኒዝሂ ኖቭጎሮድ ከተማ የሚኖረው ባለቤት አልባ ውሻ በጣም ወፍራም ከመሆኑ የተነሳ ብድግ ብሎ መነሳት እንዳልቻለ እንኳን ተነግሯል።
የዓለማችን ትልቁ የውሻ ዝርያ ከዚህ ቀደም የተመዘገበው ታላቁ ዴን ከ 136 ኪ.ግ እስከ 181 ኪሎ ግራም የሚመዝን ነበር።ነገር ግን መካከለኛ መጠን ያለው ባለቤት አልባ ውሻ 100 ኪሎ ግራም መመዘኑ ለሚሰማው በሙሉ እንግዳ ነገር ነው።
በሩሲያ ኒዝሂ ኖቭጎሮድ የሚኖሩ በጎ ፈቃደኞች በቅርቡ ይህንን ውሻ ያገኙት በየምሽቱ በህመም ሲጮህ እና በመገጣጠሚያ ህመም ምክንያት በአራት እግሮቹ ለመነሳት ሲቸገር ታይቷል። ክብደቱ የሚመለከተውን ሰው በሙሉ እንዳስገረመ ተዘግቧል። ክሩጌትስ ክብደቱ 99.9 ኪሎ ግራም ሲሆን እንዴት እንዲህ ከባድ ውፍረት ሊኖረው እንደቻለ አልታወቀም።
በአሁኑ ጊዜ በውሻው ላይ የአመጋገብ ባለሙያዎች ምርመራ አድርገዋል። የደም ናሙና የተወሰደ ሲሆን የኢንዶሮኒክ በሽታ አምጪ ተህዋስያንን ለማስወገድ ተጨማሪ ምርመራዎች ያስፈልጋሉ ሲል የውሻው ክሩጌትን በጎ ፈቃደኞች መካከል አንዱ ማብራሪያ ሰጥቷልል ። ከመጠን በላይ ሊወፍር የቻለው ምናልባት ሰዎች ብዙ ጊዜ የውሻ ትራፊዎች በሚጥሉበት በተጨናነቀ ገበያ ዙሪያ መገኘቱ ሊሆን ይችላል ተብሏል።
በውሻው ላይ ሙሉ ምርመራ ለማድረግ ፈጽሞ የማይቻል ነው በማለት በበጎ ፈቃደኞቹ ይናገራሉ።ኤክስሬይ ምርመራ በውሻው ላይ ለማድረግ ቢያንስ 50 ኪ.ግ ክብደት ሊኖረው ይገባል።ክሩጌትን በእንስሳት ሕክምና ሆስፒታል ውስጥ ማቆየት በራሱ ችግር የሆነ ሲሆን ተቋሙ በቀላሉ ውሻውን ለማሳረፍ በቂ ቦታዎች የሉትም።
የውሻውን አስፈላጊ አመጋገብ ለመጠበቅ እና የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን ለመስጠት በበጎ ፈቃደኞች በጀት ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ይገኛል። ነገር ግን ወጪው ቢበዛ እንኳን ክሩጌትን መተው እንደማይችሉ የተናገሩ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ በእርግጠኝነት አሁን ባለው ሁኔታ ክረምቱን ማለፍ አይችልም ሲሉ ሰግተዋል።ክሩጌት አሁንም በየቀኑ የህመም ማስታገሻ መድሃኒት እንደሚያስፈልገው ተናግረዋል።
አሁን ላይ እየተደረገለት ባለው እንክብካቤ ክብደት መቀነስ ቢጀምር እና በራሱ መነሳት ቢችልም አሁንም መንቀሳቀስ ስላልቻለ በጋሪ ላይ መግፋት ይኖርበታል። መነጠልን የሚወድ ውሻ ቢሆንም በአሳዳጊዎቹ ላይ ምንም አይነት የጥቃት ምልክት አላሳየም።
የውሻዎን ህይወት ለመታደግ በርካቶች እጃቸውን እየዘረጉ ሲሆን ይህ ውሻ እድሜው ገና አምስት ዓመት መሆኑ ተመላክቷል።
በስምኦን ደረጄ