
???? የተዘረፉት 4 ሚሊዮን ዶላር ቢሆንም ምንጩ ከየት ነው እንዳይባል የተሰረቁትን ገንዘብ መጠን ቀንሰዋል
እ.ኤ.አ በ2020 በደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ፋላ ፋላ እርሻ ውስጥ በሶፋ ትራስ ተሞልቶ ከነበረው የውጭ ምንዛሪ ስርቆት ጋር በተያያዘ ሁለት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።ተጠርጣሪዎቹ በዛሬዉ እለት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።የፖሊስ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ካትሌጎ ሞጋሌ ሶስተኛ ሰው ለመያዝ እየተንቀሳቀሰ ስለመሆኑ ገልጿል፡፡
“ፋርምጌት” የሚል ስያሜ የተሰጠዉ ይህዉ ውዝግቡ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ የሆነዉ የሀገሪቱ የመንግስት ደህንነት ኤጀንሲ የቀድሞ ኃላፊ አርተር ፍሬዘር ባለፈው አመት በፕሬዚዳንት ራማፎሳ ላይ የወንጀል ክስ ባቀረቡበት ወቅት ነው።ፍሬዘር ፕሬዚዳንቱን ከእርሻቸው 4 ሚሊየን ዶላር የሚገመት ተዘርፏል መባሉን ተከትሎ ነዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ፕሬዚዳንቱን በጉቦ፣ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ወንጀል በመደበቅ ተከሰዋል።
ፕሬዝዳንት ራማፎሳ የተሰረቀው ከፍተኛ የገንዘብ መጠን ተከትሎ ለመደበቅ ሲሉ ለፖሊስ አላሳወቁም በሚል ተወንጅለዋል፡፡ራማፎሳ ስርቆቱን አረጋግጠዋል ነገር ግን የተዘረፈው የሀብት መጠን 580ሺ የአሜሪካን ዶላር ነው 4 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር አይደለም ሲሉ ይፋ በተደረገዉ አሃዝ ላይ ተከራክረዋል። ገንዘቡ የተገኘው የደቡብ አፍሪካ የዱር አራዊት ኃብት የሆነ ጎሽ በመሸጥ ነው ተብሏል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በሰኔ ወር ውስጥ የህዝብ እንባ ጠባቂ በኩል ከማንኛውም ጥፋት ነጻ ተብለዋል።ራማፎሳ በ2018 ሙስናን ለመቅረፍ ቃል በመግባት ወደ ስልጣን ወጥተዋል።በስልጣን ዘመናቸው በበርካታ የወንጀል ክስ ስማቸዉ የጠፋዉን ጃኮብ ዙማን ተክተዋል።
በስምኦን ደረጄ