መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 28፤2016 –መንፈሳዊ ትምህርት እሰጣለሁ በሚል ሰበብ ሶስት የ8 ዓመት ህፃናት ለመድፈር የሞከረው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ

በማእከላዊ ኢትዮጲያ ክልል በጉራጌ ዞን ቸሀ ወረዳ በተለያዩ ቀናት ሶስት የ8 ዓመት  ህፃናት ለመድፈር የሞከረው ግለሰብብ በ14 ዓመት ከ5 ወራት ፅኑ እስራት እና አምስት መቶ ብር መቀጣቱ ተነግሯል ፡፡

ተከሳሽ አ/ቶ ናስር ከድር በጉራጌ ዞን ቸሀ ወረዳ ውረርበር ቀበሌ ልዩ ስሙ ውረርበበር ቁጥር 1 መንደር ነዋሪ ሲሆን በተለያዩ ቀናቶቹ  ኃይማኖታዊ ስርዓት በሚሰጥበት ስፍራ ዉስጥ መንፈሳዊ ትምህርት እሰጣለሁ በሚል ሰበብ 1ኛ ሀስና ሲራጅ ፣ 2ኛ መሪማ መሀመድ ፣ 3ኛ  ነኢማ ሀጅመካ የተባሉ የ8 አመት እድሜ ያላቸው ህጻናትን በተለያዩ ቀናት መንፈሳዊ ትምህርት እንዲገባችሁ ተኙ በማለት  የአስገድዶ መድፈር ሙከራ እንደፈፀመ ተገልፃል ፡፡

ግለሰቡ የከሳሽ ወላጆች ለፖሊስ ባሳወቁት መሰረት ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ያጣራው የምርመራ መዝገብ ተቀብሎ የቸሀ ወረዳ ዓቃቤ ህግ የመሰረተውን  ክስ የተመለከተው የወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳሽን ጥፋተኛ ሲል ውሳኔ አስተላልፏል ፡፡ ስለሆነም ተከሳሽ አ/ቶ ናስር ከድር በ14 አመት ከ 5 ወር ጽኑ እስራት እና 500 መቶ ብር እንዲቀጣ መወሰኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ሃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

በተመሳሳይ  አ/ቶ ማህሙድ ደሊል የተባለ ተከሳሽ  በጉራጌ ዞን ቸሀ ወረዳ በመገናሴ ከተማ በተለምዶ ሰላም ሰፈር ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ነሀሴ 27 ቀን 2015 ዓ.ም  የ4 አመት ማህሌት ታደሰ የተባለች ህፃን አታሎ በመያዝ ሰው በሌለበት ቤት ዉስጥ በማስገባት  ሊደፍራት ሲል ህፃኗ ባሰማችዉ ጩኸት ሌሎች ሰዎች ሰምተዉ ቦታዉ ሲደረሱ  ጥሏት መሄዱ ተገልፃል ፡፡

በዚህም መሰረት ፖሊስ  ተጠርጣሪዉን  በቁጥጥር ስር ያጣራው የምርመራ መዝገብ ተቀብሎ የቸሀ ወረዳ ዓቃቤ ህግ የመሰረተውን  ክስ የተመለከተው የወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳሽ አ/ቶ ማህሙድ ደሊል ጥፋተኛ ሲል  በ10 አመት ጽኑ እስራት እዲቀጣ ወስኗል፡፡

በአበረ ስሜነህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *