በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ቡልድግሉ ወረዳ ቢላጋንዳ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው ወ/ሮ አሚሳ ባባክር 3 ልጆዎችን በሰላም ተገላገለች መባሉን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል። በአሁኑ ሰዓት እናት እና ልጆች በቡልድግሉ ወረዳ ጤና ጣብያ ባለሙያዎች ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑ ተነግሯል።
የወረዳዉ ሴቶች ፣ ወጣቶችና ህጻነት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሰይዳ ኢብራሂም ለ3ቱም ህፃናት ና ለእናታቸው ሙሉ የአልባሳት ድጋፊ የተደረገ ሲሆን በቀጣይም የተቀናጀ ክትትል እና ድጋፊ እንደሚደረግ ተናግረዋል።