መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 30፤2016 –የሉዊስ ዲያዝ አባት ከኮሎምቢያ ሽምቅ ተዋጊዎች እጅ ተለቀቁ

ትውልደ ኮሎምቢያዊው የሊቨርፑል እግር ኳስ ተጫዋች የሉዊስ ዲያዝ አባት ከ13 ቀናት በፊት በግራ ክንፍ ታጣቂዎች መታገታቸው የሚታወስ ሲሆን ከእስር መፈታቱን የፖሊስ ምንጮች እና የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ሉዊስ ማኑዌል ዲያዝ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣናት እና ለካቶሊክ ቤተክርስትያን አመራሮች በብሄራዊ ነፃ አውጪ ጦር (ኤልኤን) አባላት ተላልፏል።

በምዕራባውያኑ የቀን አቆጣጠር መሰረት ጥቅምት 28 በተጫዋቹ ቤተሰብ የትውልድ ከተማ ባራንካስ ታፍነዋል። የእግር ኳስ ተጫዋቹ እናትም በቁጥጥር ስር ውለዋል የነበረ ቢሆብም በሰአታት ውስጥ ነጻ ወጥተዋል።ዲያዝ በወታደራዊ ሄሊኮፕተር ወደ ቫሌዱፓር ከተማ በመጓዝ ወደ ቤተሰቡ ከመቀላቀላቸው በፊት የህክምና ምርመራ እንደተደረገላቸው የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙና የከፋ እንግልት ሳይደርስባቸው መመለሳቸው ባለስልጣናትን ተናግረዋል። ኤል ቲምፖ ጋዜጣ እንደዘገበው፣ ጥንዶቹ በሚኖሩበት ሰፈር ውስጥ በርካታ ሰዎች ወደ ጎዳና በመውጣት ደስታቸውን ገልፀዋል። አብዛኞቹ የሊቨርፑል ቡድን ማሊያ በተለይም 23 ለብሰው ታይተዋል። የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ ዩርገን ክሎፕ ለቲኤንቲ ስፖርት እንደተናገሩት የእግር ኳስ ተጫዋቹ ዲያዝ በእውነት ደስተኛ ሆኗል ብለዋል ።

ክለቡ በትዊተር ገፁ ላይ የሉዊስ ዲያዝ አባት በደህና መመለሳቸውን በሰማነው ዜና ተደስተናል ሲል አጋርቷል። የእግር ኳስ ተጫዋቹ አባት የአጎት ልጅ የሆነው ሉዊስ አልፎንሶ ዲያዝ ለካራኮል ራዲዮ እንደተናገረው “ከብዙ የሀዘን ቀናት በኋላ ነፃ በመውጣታቻው ስሜታዊ ያደርጋል” ብሏል። “ትልቅ እርካታ ተሰምቶናል፣ መከራው በማለቁ ደስ ብሎናል” ሲል አክሏል። ፕሬዝዳንት ጉስታቮ ፔትሮ በቀድሞው ትዊተር በአሁኑ ኤክስ ላይ ባጋሩት መልዕክት “ነፃነትና ሰላም ለዘላለም ይኑር” ሲሉ ፅፈዋል።

የኮሎምቢያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለሉዊስ ማኑኤል ዲያዝ ከእስር እንዲፈቱ ለሰሩት መንግስትን፣ ወታደራዊ ሃይሎችን እና ፖሊስን ጨምሮ ምስጋናውን አቅርቧል።እገታውን የፈፀመው የኮሎምቢያው የሽምቅ ቡድን ኢኤልኤን እኤአ ከ1964 ዓ.ም ጀምሮ የትጥቅ ትግል እያደረገ የቆየ ሲሆን 2,500 አባላት እንዳሉት ይገመታል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *