መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 30፤2016 –የሶማሊያ ፕሬዝዳንት በአቡዳቢ የትከሻ ቀዶ ህክምና ተደረገላቸው

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የተሳካ የትከሻ ቀዶ ህክምና ማድረጋቸውን የፕሬዚዳንቱ ፅህፈት ቤት ገልጿል። ፕሬዝዳንት መሀሙድ ከቀላል የቀዶ ህክምና በኃላ በጥሩ ሁኔታ እያገገሙ ነው ሲል ቢሮው  ገልጿል።

በትከሻው ላይ ስላገጠማቸው የጤና ሁኔታ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃን ግን አልሰጠም። ፕሬዝዳንቱ በአቡ ዳቢ ለተወሰኑ ቀናት መቆየታቸውንና የኤምሬትስ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ማነጋገራቸውን መንግስታዊው የሶማሊያ ብሄራዊ ዜና አገልግሎት (ሶና) ዘግቧል።

ከህክምናቸው በኃላ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሪያድ የተጓዙ ሲሆን በሳውዲ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ። መሃሙድ ባለፈው አመት በድጋሚ ከተመረጡ በኋላ መንግስታቸው በአልሸባብ ላይ ለሚያካሂደው ጥቃት ድጋፍ ለማግኘት የባህረ ሰላጤ ሀገራትን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ጉዞ አድርገዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *