መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 3፤2016-የቀድሞ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን ባልተጠበቀ ሁኔታ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

የወቅቱ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ካቢኔያቸውን ሲያዋቅሩ የቀድሞ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን ባልተጠበቀ ሁኔታ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አድርገው ሾመዋል።

ከ2010 እስከ  2016 መካከል ባለው ጊዜ ውስጥ የቀድሞው የወግ አጥባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ መንግሥት መመለስ አስደናቂ ነው ሲሉ በርካቶች ገልፀዋክ ። ካሜሮን በሱናክ በተደረጉ “አንዳንድ የግለሰብ ውሳኔዎች” ባይስማሙም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠንካራ እና ብቁ መሪ ናቸው ብለው ያምናሉ።ላለፉት ሰባት ዓመታት ከግንባር ቀደም ፖለቲካ ስፍራ ውጪ ብቆይም እንደ ወግ አጥባቂ መሪ እና ለስድስት ዓመታት ጠቅላይ ሚኒስትር  እንደነበረ ሰው- ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለመርዳት ልምዴ ይረዳኛል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል።

ለአጭር ቀናት የብሪታኒ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበረችው ቴሬዛ ሜይ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው ደስታ እንደተሰማት ገልፃለች “በዓለማችን ላይ እርግጠኛ ባልሆነበት በዚህ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ታላቅ ልምድ እጅግ ጠቃሚ ይሆናል” ስትል ጽፋለች። “እንደገና አብሮ ለመስራት በጉጉት እንጠባበቃለን!” ስትል ሜይ አሳውቃለች።

ዴቪድ ካሜሮን አኤአ እ.ኤ.አ. በ 2010 ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት በ 43 ዓመታቸው የነበረ ሲሆን ከ 1812 ጀምሮ  በእንግሊዝ ታሪክ በእድሜ ትንሹ ፅህፈት ቤቱ የተረከቡ ሰው ያደርጋቸዋል በስልጣን ላይ 6 አመታትን ያሳለፉት እና የብሪ ኤክዚት ወይም የብሪታኒያን ከአውሮጳ ህብረት የመነጠል ህዝበ ውሳኔ ጫፍ እንዲደር ያደረጉ መሪ ናቸው በሚል ይታወሳሉ። በዓመቱ በተካሄደው ምርጫ በአጠቃላይ አብላጫ ድምፅ ከማግኘቱ በፊት፣ እስከ 2015 ድረስ ከሊብ ዴምስ ጋር በመተባበር ጥምር መንግሥትን መስርተዋል

ሱናክ አስቀድሞ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ፀሃፊን ሱኤላ ብራቨርማንን ከቀናት በፊት ማሰናበታቸው የሚታወስ ሲሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ጀምስ ክሌቨርሊ በብራቨርማንን ቦታ ተክተዋል።ይህ የካቢኔ ለውጥ የመጣው ሱኤላ ብራቨርማን ዋ ከስራ መባረሯን ተከትሎ ነው። በታይምስ ጋዜጣ ላይ የሜት ፖሊስን በመተቸት አወዛጋቢ መጣጥፍ ከፃፈች ከቀናት በኋላ ነው።  በጽሁፉ ላይ ለውጦች ለማድረግ ከነምበር 10 የተሰጠውን ምክር ችላ ማለቷ ተረጋግጧል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *