መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 5፤2016 – በሳውዲ አረቢያ የሀጅ ስነስርዓት ለማድረገ ሲጓዙ የነበሩ ናይጄሪያውያን አየር ላይ ቪዛቸው በመሰረዙ በግድ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ወደ ሳዑዲ አረቢያ በረራ ላይ የነበሩ ከ170 በላይ ናይጄሪያውያን ሰኞ እለት ሳወዲ እንደደረሱ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርገዋል።

ለተጓዦቹ የሳዑዲ ባለስልጣናት ቪዛቸውን በድንገት መሰረዙን መናገራቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ከናይጄሪያ ሌጎስ እና ካኖ ከተሞች ተነስተው የነበሩ 264 መንገደኞች ከመሳፈራቸው በፊት ቪዛ ተቀብለው ከባድ ምርመራ ማድረጋቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል።

ነገር ግን ሁሉም ቪዛ በአየር ላይ በነበሩበት ወቅት መሰረዙ ተነግሯል። ሲደርሱ የሳዑዲ ባለስልጣናት ወደ ናይጄሪያ እንዲመለሱ ለናይጄሪያ ኤር ፒስ አየር መንገድ ትእዛዝ ማስተላለፉ ተሰምቷል። የሳውዲ ባለስልጣናት በጉዳዩ ላይ የሰጡት አስተያየት የለም።

መጉላላት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎች ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሀገር ለመግባት የሚያስፈልጉትን ነገሮች በሙሉ በማሟላታቸው  ቪዛ መሰረዙን ሰምተው እንዳስገረማቸው ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። ሳውዲ አረቢያ የናይጄሪያ ኤምባሲ ጣልቃ ከገባ በኋላ በስተመጨረሻ ወደ 87 መንገደኞች እንዲገቡ ፈቅዳለች ቢባልም 177ቱ ሰኞ ምሽት ወደ ናይጄሪያ ተመልሰዋል።

የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን እንደገለፁት አብዛኞቹ ተሳፋሪዎች ሀጅ ለማድረግ ወደ መካ ከተማ ሳዑዲ አረቢያ ተጉዘዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *