???????? ከዚህ ቀደም ከተጠቀሰዉ 300 ሺህ የፓስፖርት ፈላጊ ሰዎች ቁጥር ወደ 190 ሺህ መቀነስ ተችሏል ተብሏል
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አዲስ አመራር ከተሾመለት ወዲህ ተቋሙ በተለያዩ የሪፎርም ስራዎች ዉስጥ መቆየቱን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት መናገራቸውን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።
ተቋሙ ከዚህ ቀደም በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ በኢትዮጵያ 300 ሺህ የፓስፖርት ፈላጊ ሰዎች ወረፋ በመጠባበቅ ላይ ናቸዉ ብሎ የነበረ ሲሆን ባለፉት ሶስት ወራት ባከናወነዉ ስራ የፓስፖርት ፈላጊ ሰዎችን ቁጥር ወደ 190 ሺህ ዝቅ ማድረግ መቻሉን አስታዉቋል።
ዋና ዳይሬክተሯ ሰላማዊት ዳዊት ፤ ባለፉት ሶስት ወራት ተቋማቸዉ 531 ሺህ 800 ፓስፖርት ከዉጭ አሳትሞ ወደ ሀገርቤት ማስገባቱን ጠቅሰዋል። ተቋሙ በአዲስአበባ ለሚገኙ ደምበኞቹ ቅድሚያ የሰጠ ሲሆን በዚህም 43 ሺህ 366 ሰዎች ፓስፖርት አግኝተዋል ብለዋል። በሌላ በኩል 15 ሺህ 793 የአስቸኳይ ፓስፖርት ፈላጊዎች አገልግሎቱን እንዳገኙም ተናግረዋል።
አገልግሎቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለዉ አሰራርም በክልል ለሚገኙ ቅርንጫፎች ፥ አዲስ አበባ ከሚገኘዉ ዋና መስሪያቤቱ የታተሙ 8 ሺህ 500 ፓስፖርት በህጋዊ መንገድ ወደ ዉጪ ለሚጓዙ ዜጎች መላኩንም ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል።
በተጨማሪም በውራቱ 38 የተቋሙ ሰራተኞች በዉጪ ከሚገኙ 15 ደላሎች ጋር በመመሳጠር ሲሰሩ ተገኝተዉ ተቀሙ ለህግ ተላለፈዉ እንዲሰጡ ማድረጉንም አክለዋል።
ሌላዉ ተቋሙ አዲስ በጀመረዉ አሰራር ለ 29 ሺህ 442 ሰዎች በተንቀሳቃሽ ስልኮቻቸዉ የአጭር የጽሁፍ መልዕክትን በመጠቀም የፓስፖርት መቀበያ ቀናቸዉን ያሰወቀ እና የተቀበሉ ሲሆን ፤ 15 ሺህ 924 የሆኑ ደምበኞች ግን በመልዕክቱ መሰረት ፓስፖርታቸዉን አልወሰዱም ብለዋል። በስተመጨረሻም አመልካቾች በሚደርሳቸዉ አጭር የጽሁፍ መልክት መሰረት ፓስፖርታቸዉን መቀበል ግዴታቸዉ መሆኑንም ዳይሬክተሯ መናገራቸውን ብስራት ራዲዮ ቴሌቪዥን ሰምቷል።
በበረከት ሞገስ