መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 8፤2016 – ነገ ለሚካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጲያ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ!

በታላቁ ሩጫ በኢትዬጲያ አዘጋጅነት በከተማችን አዲስ አበባ የሚካሄደው የሩጫ ውድድር ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው 10 ኪሎ ሜትር ውድድር ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ፤

???? ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ ሃያ ሁለት ዘሪሁን ህንፃ ላይ፣

???? ከቦሌ መድሀኒአለም ወደ ኡራኤል አትላስ መብራት ላይ፣

???? ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ፣

???? ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ መኪና አጎና ሲኒማ ለሌሎች ተሽከርካሪዎች  ጥላሁን አደባባይ ላይ፣

???? ከጎፋ ማዞሪያ አዲሱ መንገድ ወደ ለገሀር ጨርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛው ላይ፣

???? ከቡልጋሪያ ወደ ሜክሲኮ ከባድ መኪና ቡልጋሪያ መዞሪያ ሌሎች ገነት ሆቴል ላንድማርክ ላይ፣

???? ከአፍሪካ ህብረት ወደ ንግድ ምክር ቤት ጠማማ ፎቅ ላይ፣

???? ከሳርቤት ወደ ሜክሲኮ አፍሪካ ህብረት ጥይት ቤት፣

???? ከጦር ኃይሎች ወደ ሜክሲኮ ክፍተኛ ፍርድ ቤት ላይ፣

???? ከኑር ህንፃ ባልቻ መስቀለኛ ኑር ህንፃ አካባቢ፣

???? ከተስፋ ኮከብ ት/ቤት ወደ ልደታ ኮንዶምኒየም ተስፋ ኮከብ ት/ቤት ላይ፣

???? ከፈረሰኛ ወደ ጌጃ ሰፈር ፈረሰኛ መብራት ላይ፣

???? ከሞላ ማሩ ወደ ጌጃ ሰፈር ሞላ ማሩ ላይ

???? ከበርበሬ በረንዳ ወደ አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በርበሬ በረንዳ፣

???? ከጎማ ቁጠባ ወደ አረቄ ፋብሪካ ፣ወደ ሰንጋ ተራ እንዲሁም ወደ ብሄራዊ ቴአትር ጎማ ቁጠባ ላይ፣

???? ከሜትሮሎጂ ወደ ፖስታ ቤት ሜትሮሎጅ ላይ፣

???? ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢሚግሬሽን ጥቁር አንበሳ ሼል ላይ፣

???? ከጎላ ሚካኤል ወደ ኢሚግሬሽን ጎማ ቁጠባ መስቀለኛ ላይ፣

????  ከቸርቸር ወደ ለገሀር ቴዎድሮስ አደባባይና ኢሚግሬሽን መብራት ላይ፣

???? ከንግድ ማተሚያ ፣ኦርማ ጋራዥና ፍል ውሃ ንግድ ማተሚያ (ኦርማ ጋራዥ)፣

???? ከአራት ኪሎ ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፓርላማ መብራትና የድሮው አሮጌ ቄራ መስቀለኛ (ኮንሰን ላይ)፣

???? ከአዋሬ ሴቶች አደባባይ ወደ ካሳንቺስ ቶታል ሴቶች አደባባይ ላይ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናል፡፡  

ውድድሩ በሚያሄድባቸው መንገዶች ላይ ከዋዜማ ጀምሮ ለረዥም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሸከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፅሞ የተከለከለ መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ እያስታወቀ ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *