የማዳጋስካር የወቅቱ ፕሬዚደንት አንድሪ ራጆኤሊና ባለፈው ሐሙስ በተካሄደው ምርጫ በአንዳንድ ፓርቲዎች ምርጫው ውድቅ ቢደረግም 37 በመቶው የመራጮች ድምጽ ከድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ተቆጥረዋል።
እስካሁን ባለው ውጤት መሰረት ፕሬዝዳንት ራጆኤሊና በ62.4 በመቶ የመራጮችን ድምፅ በማግኘት ይመራሉ። ተቀናቃኛቸው ራንድሪአንሶሎኒኮ በ12.2 በመቶ የመራጮችን ድምፅ ሲያገኙ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ማርክ ራቫሎማናናን በ11.2 በመቶኛ ድምፅ በማግኘት ይከተላሉ።
እስካሁን በተደረጉት የምርጫ ጣቢያዎች ቆጠራ መሰረት የማዳጋስካር የምርጫ ኮሚሽን እንዳስታወቀው ድምፅ ከሰጡት የመረጡት 43 በመቶ ያህል መሆናቸውን አስታውቋል።ከፕሬዝዳንታዊ ውድድሩ ራሳቸውን ያገለሉ አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲ እጩዎች መራጮች በምርጫው እንዳይሳተፉ ባደረጉት ጥሪ ለተመዘገበው ዝቅተኛ የመራጮች ተሳትፎ ምክንያት ሆኗል።
ምርጫው የሚጠበቀውን የዲሞክራሲ ደረጃዎች አላከበረም እናም ይህ በማዳጋስካር የምርጫ ታሪክ ውስጥ ዝቅተኛው የህዝብ የተሳትፎ መጠን የታየበት ነው ሲሉ የተቃዋሚ ፖለቲከኛ ሃጆ አንድሪያናሪቬሎ ሐሙስ እለት መናገራቸው ይታወሳል። የምርጫው ቅድመ ዝግጅት በሁከትና ብጥብጥ የታጀበ ሲሆን ከ 12 ተቃዋሚ ፕሬዚዳንታዊ እጩዎች መካከል 10ሩ የምርጫውን ሂደት ውድቅ አድርገዋል።
ፕሬዝዳንት ራጆኤሊና የፈረንሳይ ጥምት ዜግነት ያላቸው መሆኑን ፖለቲከኞቹ ውድቅ አድርገዋል። የፕሬዚዳንት ራጆኤሊናን ለሶስተኛ የስልጣን ዘመን በድጋሚ መወዳደር በማውገዝ በምርጫው ተዓማኒነት ላይ ስጋት ፈጥሯል። ምርጫው ሊደረግ ባሉት ሳምንታት ውስጥ ከፖሊስ ጋር ሰልፎች ግጭት ውስጥ ገብተዋል።
በዋና ከተማዋ አንታናናሪቮ በምርጫው ዋዜማ የሰዓት እላፊ እገዳ ተጥሎ እንደነበር ይታወሳል።
በበረከት ሞገስ