
???? ከስፔናዊ ወንድ ጋር ገና ፍቅር ስጀምር እንዴት ገንዘብ እንደሚሰበስብ የገቢዎች ቢሮ ምራቁን ሲውጥ ነበር ስትል ሻኪራ ተናግራለች
ኮሎምቢያዊቷ የፖፕ ኮከብ ድምፃዊት ሻኪራ የክስ ሂደቱ ሊጀመር በቀረበበት ወቅት የታክስ ማጭበርበር ጉዳይን ለመፍታት ከስፔን አቃብያነ ህጎች ጋር ስምምነት ላይ ደርሳለች።
ድምፃዊቷ በባርሴሎና ፍርድ ቤት የ14.5 ሚሊዮን ዩሮ የሚደርስ የታክስ ማጭበርበር ክስ ቀርቦባት ነበር። የስፔን አቃብያነ ህጎች ጥፋተኛ ሆና ከተገኘች ለስምንት አመታት እስራት እና ድምፃዊቷን 23.8 ሚሊዮን ሊቀጡ ፈልገው ነበር። ምንም አይነት ጥፋት እንዳልሰራች በተደጋጋሚ ክሱን የምትግደው ሻኪራ “በልጆቼ ፍላጎት” የተነሳ በስምምነት እንዲቋጭ መስማማቷን ተናግራለች።
አክላም “እናታቸው በዚህ የፍርድ ቤት ክርክር የግል ደህንነቷ ሲጣስ ማየት አይፈልጉም” ብላለች ።ሻኪታ ከዚህ ቀደም በአቃቤ ህግ የቀረበለትን የእንስማማ ጥረ ውድቅ አድርግም የነበረ ሲሆን ይልቁኑ ጉዳዩ ለፍርድ መቅረብን መርጣለች።በሙያዬ ሁልጊዜ ትክክል የሆነውን ለማድረግ እና ለሌሎች መልካም ምሳሌ ለመሆን እጥር ነበር። በዚህ ሂደት ውስጥ አማካሪዎቼ የነበሩትን የአለም ዋና የታክስ ባለስልጣናት ፕራይስዋተርሃውስ ኢንተርናሽናል ሊሚትድ እና ኧርነስት ኤንድ ያንግ ግሎባል ሊሚትድ ምክር መጠየቅን ጨምሮ ፍጹም ምርጥ ምክር ለማግኘት በንግድ እና በግል የገንዘብ ውሳኔዎች ላይ ተጨማሪ እርምጃ ለመውሰድ ችያለሁ ስትል ሻኪራ ተናግራለች።
የውዝግቡ መነሻ የሻኪራ ነዋሪነት ስፍራ ሲሆን ከ2012 እስከ 2014 ባሉት ዓመታት አቃብያነ ህጎች እንደመሉት በስፔን እንደምትኖር መረጃዎች ያሳያሉ። በስፔን ህግ መሰረት ደግሞ ከስድስት ወራት በላይ በሀገሪቱ ውስጥ የሚያሳልፉ ሰዎች እንደ ነዋሪ ስለሚቆጠሩ ግብር እንዲከፍሉ ይጠሸቃል። ነገር ግን ሻኪራ በወቅቱ ስፔን በዋናነት የምትኖርበት ቦታ እንዳልነበረ ትከራከራለች።
አቃቤ ህግ እንደሚለው በ2012 በባርሴሎና ውስጥ ቤት እንደገዛች የሚገልጽ ሰነድ አውጥቷል
ይህም ለእርሷ እና በጊዜው የትዳር አጋሯማ የባርሴሎና እግር ኳስ ተጫዋች ለነበረው ጄራርድ ፒኬ የቤተሰብ ቤት ሆኖ አገልግሏል። እ.ኤ.አ. እስከ 2014 ድረስ አብዛኛው የሻኪራ ገቢ ከአለም አቀፍ ጉብኝቶች የመጣ እና ከስፔን ውጭ ብዙ ጊዜ እንዳሳለፈች ጠበቆቿ ግን ተከራክረዋል። የስፔን የግብር ባለሥልጣናህ ከስፔን ዜጋ ጋር የፍቅር ግንኙነት ስጀምር እንዴት ታክስ መሰብሰብ እንዳለባቸው አስበው ምራቃቸውን መዋጥ ጀምረው ነበር ስትል ሻኪራ ገልፃለች።
ምንም ቢሆን ያንን ገንዘብ ለማግኘት እንደሚፈልጉ ግልጽ ነው ስትል ለኤሌ መጽሔት ተናግራለች። ሻኪራ እ.ኤ.አ. በ 2015 ስፔንን የግብር አገልግሎት ለመኖሪያ ቦታዋ 17.2 ሚሊዮን ዩሮ ታክስ እንደከፈለች እና ምንም ዓይነት ዕዳ እንደሌለባት ተናግራለች። እ.ኤ.አ. በ2019 በተለየ ጉዳይ ፒኬ ከ2008 እስከ 2010 ታክስ በማሸሽ በሚል ወንጀል በስፔን ብሄራዊ ፍርድ ቤት 2.1 ሚሊዮን ዩሮ ተቀጥቶ ነበር።
ጥንዶቹ ከ11 ዓመታት የጋብቻ ቆይታ በኋላ መለያየታቸውን በሰኔ ወር ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። የትዳር ዘመናቸው የሰባት እና የዘጠኝ አመት እድሜ ያላቸው ሁለት ወንዶች ልጆች አፍርተዋል።
በስምኦን ደረጄ