መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 11፤2016 – በሀላባ ዞን ዱባይ እልካለሁ በማለት ሲያታልል የነበረዉ ደላላ በ12 ዓመት ፅኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን አንዲት ግለሰብን ወደ ዱባይ ሀገር እልካለሁ በሚል አታሎ 24 ሺህ የተቀበለ ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ በፅኑ እስራትና በገንዘብ መቀጣቱ ተነግሯል ።

ተከሳሽ ሙሂዲን መሀመድ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለራሱ ለማግኘት በማሰብ የግል ተበዳይ የሆነችውን ከድጃ ከያቶን ወደ ዱባይ እልክሻለሁ በማለት አታሎ 24 ሺህ ብር በመቀበሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ሃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

ፖሊስ ያጣራውን የምርመራ መዝገብ ተቀብሎ አቃቤ ህግ የመሠረተውን ክስ የተመለከተው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተከሳሽ ላይ የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል ። ፍርድ ቤቱ ተከሳሹን ያርሟል ሌሎችን ያስተምራል በማለት በ12 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ2000 ብር የገንዘብ መቀጮ እንድቀጣ  ዉሳኔ አስተላልፏል ።

በዞኑ በህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች  ለይ የሚወሰደው ህጋዊ እርምጃዎች ተጠናክረው ቢቀጥልም  አሁንም በርካታ ዜጎች በህገወጥ ደላሎች አማካኝነት ከሀገር ለመዉጣት በሚል ከአካል ጉዳት እስከ ህይወት ማጣት እየደረሰባቸው ይገኛል ተብሏል ።

በአበረ ስሜነህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *