መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 11፤2016 – የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ያለ ንግድ ፍቃድ ሲነግዱ የነበሩ ከ3 ሺኅ በላይ ነጋዴዎች አግኝቻለሁ ሲል አስታወቀ

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በ2016 ዓመት የመጀመሪያው ሩብ አመት ባደረገው ፍተሻ 10ሺ285 ድርጅቶች እና ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

ከነዚህም ውስጥ ያለ ንግድ ፍቃድ ሲነግዱ የነበሩ 3 ሺኅ 79 የንግድ ተቋማት እንደተገኙ ገልፀዋል፡፡ያለ ንግድ ፍቃድ ሲነግዱ ከነበሩት 3 ሺ 79 ነጋዴዎች ውስጥ በተለያዩ እርምጃዎች 2874 ነጋዴዎች ወደ ህጋዊነት እንዲመለሱ መደረጉን  የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን ተናግረዋል ፡፡

ዳይሬክተሩ  እንደገለፁት 209 ነጋዴዎች ባልታደሰ ንግድ ፍቃድ ሲነግዱ እንደተያዙ እና እርምጃ እንደተወሰደባቸው አክለዋል ፡፡ እርምጃው ከተወሰደባቸው ውስጥ 186ቱ ወደ ህጋዊነት ተመልሰዋል፡፡

በተጨማሪም ምርት በመጋዘን አከማችተው የተገኙ ነጋዴዎች መኖራቸውን በተለይም ደግሞ የኑሮ ውድነት ለማባባስ በማሰብ እጥረት ያለባቸውን ምርቶች አከማችተው የተገኙ 19 ነጋዴዎች ተገኝተዋል፡፡ ከተገኙት መካከል 18ቱ ምርቶቻቸው ወደ ገበያ እንዳይወጡ ተደርገዋል። ሌሎቹ ደግሞ ምርቶቻቸው ወደ ሸማች በመውሰድ እንዲከፋፈሉ ማድረግ መቻሉን ቢሮው አስታውቋል ፡፡

በህጉ መሰረት ነጋዴዎች ከአጠቃላይ ካፒታላቸው ከ25 በመቶ በላይ ማከማቸት እንደማይችሉ በመጥቀስ አስራ ዘጠኙ ነጋዴዎች ግን ከሚገባቸው በላይ በመጋዘን አከማችተው የተገኙ መሆናቸውን አቶ ሰውነት ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል ፡፡

በምህረት ታደሰ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *