መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 11፤2016 – ደቡብ አፍሪካ በኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ እንዲወጣ ዓለም አቀፍ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤትን ጠየቀች

የደቡብ አፍሪካ መንግስት በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ላይ እስከ ታህሣሥ አጋማሽ ድረስ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ እንዲያወጣ ጠይቋል። የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ሚኒስትር ኩምቡድዞ ንትሻቭሄኒ እንደተናገሩት ፍርድ ቤቱ ይህንን ካላደረገ የአለምአቀፍ አስተዳደር “ጠቅላላ ውድቀት” መሆኑን ያሳያል ብለዋል።

“አለም ዝም ብሎ ቆሞ ማየት አይችልም” በማለት ሚኒስትሯ አክለዋል። እስራኤል በጥቅምት 7 በሃማስ 1,200 ዜጎቿ ከተገደሉባት እና ከ200 በላይ የሚሆኑ ታግተው የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ እራሴን እየከላከልኩ ነው  ትላለች። በሲቪሎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ እየሞከርኩኝ ነው ብትልም ሚኒስትሯ ንትሻቭሄኒ የእስራኤል መንግስት “አብዛኞቹን የፍልስጤማውያንን ከጋዛ ለማፅዳት እና ለማፈናቃ” እየሞከረ ነው ብለዋል ።

ደቡብ አፍሪካ ከባንግላዲሽ፣ ቦሊቪያ፣ ኮሞሮስ እና ጅቡቲ ጋር በመሆን በጋዛ የጦር ወንጀሎች እና በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች እንዲጣራ ለፍርድ ቤቱ ጥሪ አቅርበዋል። ደቡብ አፍሪካ የፍልስጤም ጉዳይ በይፋ ደጋፊ ነች። ሀገሪቱ ዲፕሎማቶቿን ከእስራኤል ማስውጣቷን አስታውቃለች። በፕሪቶሪያ የእስራኤል አምባሳደር መኖር የማይቻል ጉዳይ እየሆነ መምጣቱን ጠቁማለች።

በሌላ በኩል ደቡብ አፍሪካውያን በእስራኤል እና ጋዛ ግጭት በጥልቅ መለያየት ውስጥ እንዲሆኑ መፍቀድ የለባቸውም ሲሉ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በትላንትናው እለት ሰኞ ተናግረዋል። ይህንን ሊናገሩ የቻሉት ባለፈው ሳምንት በኬፕ ታውን የእስራኤል እና የፍልስጤም ደጋፊዎች መካከል ከተቀሰቀሰው ግጭት በኋላ ነው። ፕሬዝዳንቱ ይህንን ክስተት “አስጨናቂ እና ተቀባይነት የሌለው” ሲሉ በሳምንታዊ መግለጫቸው ላይ ተናግረዋል ።

ፕሬዝዳንት ራማፎሳ እና ገዢው የደቡብ አፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ ለፍልስጤማውያን ያላቸውን አጋርነት በይፋ ገልፀዋል። ለፍልስጤም ትግል የሚደረገው ድጋፍ ከፀረ-ሴማዊነት ጋር ሊመሳሰል አይችልም ብለዋል። ራማፎሳ በመቀጠል መንግስታቸው ለፍልስጤማውያን የሚያደርገውን ድጋፍ በደቡብ አፍሪካ የአይሁድ ማህበረሰብ እንዲገለል እና ጉዳት እንዲደርስበት ማድረጉን ማሳያ ነው ሲል የእስራኤል ጋዜጣ የሰራውን ዘገባ የሀሰት ሲሉ አውግዘዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *