መደበኛ ያልሆነ

ጥር 1፤2016 – ኡጋንዳ ከአሜሪካ የንግድ ስምምነት እንድትወጣ መደረጉን ተከትሎ ሙሴቬኒ ዉሳኔዉ አይጎዳንም ሲሉ አጣጣሉት

ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ ኡጋንዳ የምስራቅ አፍሪካን ከሚያከብሩ አለም አቀፍ አጋሮች ጋር እንደምትገበያይ ተናግረዋል፡፡የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ እንደተናገሩት ዩጋንዳ ከአሜሪካ እና አፍሪካ ትልቅ የንግድ መርሃ ግብር ከተገለለች ከአንድ ሳምንት በኃላ ሀገራቸውን “ለመጫን” የውጭ ሙከራዎች ከንቱ ናቸው ብለዋል።

ኡጋንዳ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በመቃወም ጠንካራ ህግ ካፀደቀች በኋላ አሜሪካ በግንቦት ወር ኡጋንዳ ላይ ማዕቀብ እንደምትጥል እና ከአፍሪካ የእድገት እና እድል ህግ (አጎዋ) የንግድ ስምምነት እንደምታባርር ዝታ ነበር።ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ ባደረጉት ሀገራዊ ንግግር “ጫና የሚያደርጉብን ጊዜያቸውን እያባከኑ ነው።እናም ስለዛ ጉዳይ መጨነቅ የለብንም” ብለዋል፡፡

“ማተኮር ያለብን በመካከላችን ሙስናን መዋጋት ነው። እነዚህ ችግሮች ናቸው እንጂ የውጭ ጫና ችግራችን አይደለም፣ ምክንያቱም ያ ምንም ትርጉም የለውም” ሲሉም አክለዋል።ሙሴቬኒም ኡጋንዳ “ከሚያከብሯት” ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር እንደምትገበያይ ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *