መደበኛ ያልሆነ

ጥር 1፤2016 – የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ዋና ፀሀፊ የፕሮስቴት ካንሰር ቀዶ ህክምና እንደተደረገላቸው ፔንታጎን አስታወቀ

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን በታህሳስ ወር የፕሮስቴት ካንሰር ምርመራን ለማከም በተደረገ ቀዶ ህክምና ውስብስብ ችግር አጋጥሟቸዋል ሲሉ ባለስልጣናት ተናግረዋል ። ኢንፌክሽኑ ኦስቲን ከአስር ቀናት በፊት ወደ ሆስፒታል እንዲገቡ ብሎም ወደ ከፍተኛ የህክምና ክትትል  ክፍል እንዲገቡ አስገድዷቸዋል። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ስለ ኦስቲን የፕሮስቴት ካንሰር ምርመራ ብቻ እንጂ ቀዶ ህክምና ስለማድረጋቸው መረጃው አልነበራቸውም ሲል ዋይት ሀውስ አስታውቋል።

የ70 አመቱ ኦስቲን የህክምና ሂደትን ከፍተኛ ባለስልጣናት የሶስት ቀናት የሆስፒታል ቆይታቸውን እንዳልሰሙ ከታወቀ በኋላ ትችት ገጥሟቸታል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ “ህዝቡ በተገቢው መንገድ ያለውን መረጃ እንዲያውቅ” ባለማድረጋቸው ይቅርታ ጠይቀዋል።የመከላከያ ፀሀፊው ከፕሬዝዳንቱ ስር የስልጣን እርከን ላይ ይገኛሉ። ከፕሬዚዳንቱ ካቢኔ አባላት አንዱ ናቸው። ለዋይት ሀውስ ስለ ህመማቸው ለማሳወቅ መዘግየታቸው በባይደን አስተዳደር ውስጥ የብሄራዊ ደህንነት ስጋቶች እና የግልጽነት ጉዳዮችን አስነስቷል።

ፔንታጎን ኦስቲን በዛሬው እለትም ሆስፒታል እንደሚቆዩ አረጋግጧል።የፔንታጎን ቃል አቀባዩ መቼ ከሆስፒታል እንደሚወጡ መረጃ አልሰጡም።ኦስቲን በሆስፒታል ቆይታቸው ለዋይት ሀውስ እና ለከፍተኛ የፔንታጎን ባለስልጣናት ማስጠንቀቅ ባለመቻላቸው ውዝግብ አስነስቷል። የኦስቲን ምክትል ካትሊን ሂክስ አንዳንድ ኃላፊነቶቹን እንዲወስዱ ቢጠየቁም ስለሆስፒታል ቆይታቸው ለምክትላቸውም አልተነገረም።

የፕሮስቴት ካንሰር በሚሊዮን የሚቆጠሩ አሜሪካውያንን ያጠቃል፣ ከስምንቱ አሜሪካውያን መካከል አንዱ በሕይወት ዘመናቸው በሽታው ይያዛሉ ሲል የአሜሪካ የካንሰር ማኅበር መረጃ ያሳያል። በተለይ አፍሪካ አሜሪካዊያን ወንዶች ለበሽታው ይበልጥ የተጋለጡ ናቸው። በካንሰር የመጠቃት ዕድላቸው ከሌሎች ወንዶች የበለጠ ሲሆን በበሽታው የመሞት እድላቸው በእጥፍ ያህል መሆኑን የአሜሪካ ካንሰር ማህበር መረጃ አመላክቷል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *