መደበኛ ያልሆነ

ጥር 2፤2016 – በሀላባ ዞን በሳንጃ ወግተው ሞተር የነጠቁ ተጠሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን በዌራ ዲጆ ወረዳ በቁሉብ ቀበሌ ሰቦላ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በሞተር ሳይክል አሳፍሮ እየወሰዳቸው በሳንጃ ወግተው ሞተር የነጠቁ ሁለት ተጠሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል ።

ተጠርጣሪዎች ከበሸኖ ከተማ እስከ አሸሹሬ ከተማ ውሰደን በማለት ከተሳፈሩ በኋላ አሽከርካሪውን በሰንጃ አንገቱን ወግተው ሞተር ብስክሌቱን ቀምተው መውሰዳቸው ተገልጿል ።

ነገር ግን ህብረተሰቡ በአደረገው ርብርብ  ሞተሩን ማስጣል ሲቻል ተጠርጣሪዎች 
አምልጠው የነበረ ቢሆንም ፖሊስ በአደረገዉ ክትትል ሁለቱም ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ሃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል  ።

በተጠርጣሪዎች ጉዳት የደረሰበት አሽከርካሪው ከበሸኖ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሪፈረር ተደርጎ በወራቤ ኮምፕረንሲቪ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እየታከመ እንደሚገኝ ተገልጿል ። የሞተር ብስክሌት  ስርቆት ከጊዜ ወደ ጊዜ መልኩን እየቀየረ የመጣ መሆኑንና  ተገቢዉ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ተብሏል ።

በአበረ ስሜነህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *