መደበኛ ያልሆነ

ጥር 2፤2016 – በቅናት በመነሳሳት የሁለት ልጆች እናትና ባለቤቱን የገደለዉ ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ

በምራብ አርሲ ዞን ቁሬ ወረዳ ጉተማ ሰይድ የተባለ ግለሰብ  ትዳር መስርቶ እየኖረ እያለ ከሁለት ልጆች ባለቤቱ ጋር በቅናት ምክኒያት ግጭት ይፈጥራሉ።

ግለሰብም እኔ ስራ ስሄድ ከሌላ ሰዉ ጋር ትገናኛለሽ በማለት ከባለቤቱ ጋር  አለመግባባት ሲፈጠር ሚስቱም ችግሮችን ለመፍታት ብትሞክርም ሳይሳካ ይቀራል።

ግለሰቡም በቅናት ምክኒያት  በመነሳሳት ይገልና እራሷን እንዳጠፋች  በማስመሰል ይሰቅላታል።ፖሊስም እራሷን አጠፋች የሚል መረጃ ሲደርሰዉ  በመጠራጠር አቤት ሆስፒታል የአስከሬን እንዲመረመር ሲያደርግ እራሷን እንዳላጠፋች ያረጋግጣል።

ፖሊስም  ጉተማ ሰይድን በቁጥጥር ስር አዉሎ ምርመራዉን ካጣራ በኋላ ለአቃቢ ህግ ይልከዋል።አቃቢ ህግም የደረሰዉን  የሰዉና የሰነድ መረጃ በማጣራት ክስ ይመሰርታል።

ክሱን ሲመለከት የቆየዉ የምራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋለዉ የወንጀል ችሎት በ22 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ እንደዎሰነበት የሞዕራብ አርሲ ዞን የወንጀል ምርመራ ክፍል ኅላፊ ኢንስፔክተር ከድር ጅቦ ጨምሮዉ ለብስራት ቴሌቬዥንና ራዲዮ ገልፀዋል።

በበቀለ ጌታሁን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *