መደበኛ ያልሆነ

ጥር 2፤2016 – ወደ አፍሪካ ዋንጫ የሚያመራዉ የጋምቢያ ብሄራዊ ቡድን አባላት ለሞት ሊዳረጉ እንደነበር ተሰማ

በ2023 ስያሜ በሚዘጋጀዉ የአፍሪካ ዋንጫ ወደ አይቮሪ ኮስት የሚጓዘው የጋምቢያ ብሄራዊ ቡድን በአውሮፕላናቸው ላይ በደረሰው የካርቦን ሞኖክሳይድ መመረዝ “ለሞት ሊዳረጉ ይችል እንደነበር” የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ቶም ሴንትፊት ተናግረዋል።የኤር ኮትዲቫር በረራ ከጋምቢያ ዋና ከተማ ባንጁል በትላንትናዉ እለት ከተነሳ ከዘጠኝ ደቂቃ በኋላ ዳግም ለማረፍ የተገደደ ሲሆን በአውሮፕላኑ ውስጥ ኦክሲጅን ባለመኖሩ በርካታ የልዑካን ቡድን አባላት እንቅልፍ ጥሏቸዋል፡፡

ሴንትፊት የቡድኑን ደህንነት በመጠበቅ የአብራሪው ፈጣን ዉሳኔ አወድሰዋል፡፡ሴንትፊት አክለዉ እንደተናገሩት “የአዉሮፕላኑ ሰራተኞች ከመነሳታችን በፊት በአየር ማቀዝቀዣው ላይ ችግር ነበር ነገርግን ስንነሳ ጥሩ ይሆናል” ብለዉ ነግረዉን ነበር ብለዋል።ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ አውሮፕላኑ በጣም ሞቃት ሆነ።የኦክስጅን እጥረት ስለነበረ ሁላችንም እንቅልፍ ጣለን፤ ከተጫዋቾች መካከል አንዳንዶቹ ሊነቁ አልቻሉም፤ አብራሪው ሁኔታዉን ስላስተዋል ተመልሰናል ብለዋል፡፡

በበረራዉ ላይ የነበሩ ሰዎች ራስ ምታት እንደነበራቸዉ እና በረራው ለተጨማሪ 30 ደቂቃዎች ቢቀጥል ኖሮ ሁሉም የቡድን አባላት ይሞቱ እንደነበር ተገልጿል፡፡የኦክስጂን ጭምብሎች አለመውጣታቸው ደግሞ ግራ አጋቢ ሲሆን ሁሉም የብሄራዊ ቡድኑ አባላት በድንጋጤ ውስጥ ይገኛሉ፡፡አንዳንድ ተጫዋቾች በተፈጠረው ነገር የተነሳ ወደ ልምምድ መመለስ አልቻሉም። አሁንም ራስ ምታት ያለባቸዉ ሲሆን ይህ ደግሞ አሳሳቢ ነው፣ አንዳንድ ተጫዋቾች አሁንም መፍዘዝ ይታይባቸዋል ሲሉ ሴንትፊት አክለዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *