መደበኛ ያልሆነ

ጥር 2፤2016 – የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፍርድ ቤት ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ ያቀረበችውም የዘር ማጥፋት ወንጀል ክስን ተመለከተ

የተባበሩት መንግስታት አለም አቀፍ የፍትህ ፍርድ ቤት ደቡብ አፍሪካ ያቀረበችው እስራኤል በጋዛ በፍልስጤማውያን ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽማለች የሚለውን የክስ ዝርዝር ሰምቷል።

እስራኤል ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንድታቆም ፍርድ ቤቱን ደቡብ አፍሪካ ጠይቃለች። ጉዳዩ የወንጀል ችሎት ባለመሆኑ በዘር ማጥፋት ክስ ላይ አስተያየት ብቻ  ፍርድ ቤቱ የሚሰጥ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ክሱን በትኩረት ተከታትሏል። እስራኤል በደቡብ አፍሪካ የቀረበውን ክስ “መሰረተ ቢስ” ስትል አጥብቃ ውድቅ አድርጋለች። ደቡብ አፍሪካ በዛሬው እለት ክሱን ስታቀርብ እስራኤል ደግሞ መከላከያዋን በነገው እለት ታቀርባለች።

ደቡብ አፍሪካ የእስራኤል ድርጊት የፍልስጤም ጎሳ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጥፋት ለማምጣት የታለመ ነው ብላለች ። የእስራኤል ድርጊት በጋዛ ፍልስጤማውያንን መግደል፣ በአካል እና በአእምሮ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ እና አካላዊ ውድመትን ለማምጣት የተሰላ ድርጊቶችን ማድረስን ነው ሲል ያጠቃልላል።
እስራኤል በጋዛ ውስጥ ሁሉንም ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ማቆምን ጨምሮ ጊዜያዊ እርምጃዎች እንዲተገበሩ ፍርድ ቤት በአስቸኳይ ትዕዛዝ እንዲሰጥ ይጠይቃል።

የእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ የደቡብ አፍሪካን ውንጀላ “አሰቃቂ እና አስመሳይ” ሲሉ አጣጥለውታል። በዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት እንገኛለን እራሳችንን ለመከላከል የምንጠቀመውን የሰብዓዊ ህግ በኩራት እናቀርባለን ብለዋል ። አክለውም የእስራኤል ጦር ያልተፈለገ ውጤት እንዳይኖር እና በሲቪል ላይ ጉዳት እንዳይደርስ መሬት ላይ ያለውን እጅግ ውስብስብ ሁኔታዎች በማጤን የተቻለውን ሁሉ እያደረገ ነው  ብለዋል።

መቀመጫውን በኔዘርላንድ ሄግ ያደረገው ይህው ፍርድ ቤት እስራኤል ወታደራዊ ዘመቻዋን እንድታቆም ደቡብ አፍሪካ ባቀረበችው ጥያቄ ላይ ፈጣን ውሳኔ ሊሰጥ ይችላል። ነገር ግን እስራኤል የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመች ነው ወይስ አይደለም የሚለው የመጨረሻ ውሳኔ አመታት ሊወስድ ይችላል። የፍርድ ቤቱ ውሳኔዎች በንድፈ ሀሳብ ደረጃ እስራኤል እና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በፍርድ ቤቱ አባል በሆኑ ወገኖች ውስጥ ህጋዊ ናቸው ነገር ግን ተፈጻሚነት የላቸውም። እ.ኤ.አ. በ 2022 ፍርድ ቤቱ ሩሲያ በዩክሬን ውስጥ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ወዲያውኑ እንድታቆም ትእዛዝ የሰጠ ቢሆንም ትዕዛዙ ችላ ተብሏል ።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *