መደበኛ ያልሆነ

ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ የ264 ሚሊዮን ዶላር የቀላል ብድር ስምምነት መፈራረማቸው ታውቋል

የደቡብ ኮሪያ ኤክስፖርትና ኢምፖርት ባንክ (EXIM BANK) በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚከናወኑ የልማት ፕሮክቶች የሚውል የ264 ሚሊዮን ዶላር የቀላል ብድር ለማቅረብ የሚያስችል የማዕቀፍ ስምምነት በገንዘብ ሚኒስቴር ተደርጓል፡፡

የመጀመሪያው የ170 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት በደቡብ ኢትዮጵያ ለሚገኘው የብሔራዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍሰትና የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ፕሮጀክት የሚውል እንደሆነ በገንዘብ ሚኒስትር የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ የሆኑት አቶ ሃጂ ኢብሳ ለብስራት ተናግረዋል፡፡

በዚህም በሰሜን ምዕራብ ለሚገኙ የሀገሪቱ ክፍሎችና እና ለኦሞ ስኳር ፋብሪካ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሀይል ለማቅረብ ያስችላል ተብሏል፡፡

ተጨማሪም ለአርባምንጭ ኢንዲስትሪያል ፓርክ እንደሚውል ተነግሯል፡፡

የሁለተኛው የ94 ሚሊዮን ዶላር የቀላል ብድር ስምምነት በሀገሪቱ ውስጥ ለሚስሩ የመስኖ ልማትና የገጠር ልማት ፕሮጀክቶች እንደሚውል ተጠቅሷል፡፡

አርሶ አደሩ የግብርና ምርቱን እንዲያሳድግና ገቢው እንዲጨምር ያደርጋል መባሉንም አቶ ሃጂ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

 

ፍሬህይወት ታደሰ

 

መደበኛ ያልሆነ

ህገ ወጥ የጎዳና ነጋዴዎች

ከ 4ሺ በላይ ህገ ወጥ የጎዳና ነጋዴዎችን ህጋዊ የመሸጫ ቦታ ሊሰጣቸው እንደሆነ ተነገረ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ የመጣውን የጎዳና ላይ ንግድ ለማስቀረት የሚያስችል ስርዓት እየዘረጋ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል ፡፡
የጎዳና ላይ ነጋዴዎችን በአንድ አሰባስቦ በህጋዊ ስርዓት ውስጥ እንዲነግዱ ለማድረግ የሚያስችለው ቀዳሚ ተግባር በነገው እለት እንደሚከናወን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ በላይ ወልደሰንበት በተለይም ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡
ነጋዴዎቹ ቦታው የሚሰጣቸው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቦሌ እና የካ ክ/ከተማ ሲሆኑ የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ቦታው ላይ ተገኝተው ርክክቡን እንደሚያደርጎ ተገልጿል፡፡
በቀጣይም ቦታውን የተረከቡት ነጋዴችን ለመከታተል እና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ንግድ ቢሮው ከደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ፤ከአዲስ አበባ ፖሊስ እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ አቶ በላይነህ ወልደሰንበት ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል ፡፡
ህጋዊ ባልሆነ መንገድ የሚነግዱ የጎዳና ላይ ነጋዴዎች እስከ ጥቅምት ሰላሳ የምዝገባ ሂደቱን ማከናወን እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡
ናትናኤል ሀብታሙ

መደበኛ ያልሆነ

ህገ ወጥ የስንፈተ ወሲብ መድኃኒቶች በገበያ ላይ መዋላቸው ተገልጿል፡፡

ህገ ወጥ የስንፈተ ወሲብ መድኃኒቶች በገበያ ላይ መዋላቸው ተገልጾል፡፡

የኢትዮጵያ የምግብ መድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን በድህረ ገበያ ቅኝት ባደረገው የቁጥጥር ስራ ያልተመዘገቡ፣ ጥራት እና ደህንነነታቸው ያልተረጋገጡ በህገወጥ መንገድ ወደሀገር ውስጥ የገቡ የስንፈተ ወሲብ መድሃኒቶች ማግኘቱን የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሳምሶን አብርሀም ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡ መደኃኒቶች ህጋዊ መሆን አለመሆናቸውን ለመለየት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ስርዓት የዘረጋ ሲሆን ይሄም የመድኃኒቱን ስም በwww.mris.fmhaca.gov.et በሚለው ዌብሳይት በማስገባት መድኃኒቱ መመዝገብ አለመዝገቡን እና ሌሎች ከመድኃኒቱ ጋር ተየያዥነት ያላቸው መረጃዎችን ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል፡፡ ስለሆነም ማህበረሰቡ መሰል ተግባር ሲፈፀም ከተመለከተ በአከባቢያቸው ላሉት ተቆጣጣሪ አካላት አሊያም ለጤና ቢሮ እና ለፖሊስ በተጨማሪም በነጻ ስልክ መስመር 8482 በመደወል ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እንዲያሳውቅ አቶ ሳምሶን አሳስበዋል፡፡ ፍሬህይወት ታደሰ